ኤፌሶን 5:30-33
ኤፌሶን 5:29-33 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ። ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፥ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ።
ኤፌሶን 5:30-33 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እኛ የክርስቶስ አካል ብልቶች ነንና። “ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋራ ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” ይህ ጥልቅ ምስጢር ነው፤ እኔም ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እናገራለሁ። ሆኖም ከእናንተ እያንዳንዱ ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይውደድ፤ ሚስትም ባሏን ታክብር።
ኤፌሶን 5:30-33 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እኛም የክርስቶስ አካል ክፍሎች ነን፤ “በዚህ ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ” ተብሎአል። ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፤ ይህንንም የምለው ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ ነው። ነገር ግን ይህ ነገር እናንተንም ይመለከታል፤ ስለዚህ ባል ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይውደድ፤ ሚስትም ባልዋን ታክብር።
ኤፌሶን 5:30-33 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እኛ የአካሉ ሕዋሳት ነንና። “ስለዚህም ወንድ አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋር አንድ ይሆናል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ።” ይህም ምሥጢር ታላቅ ነው፤ እኔም ይህንኑ ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያኑ እናገረዋለሁ። እንግዲያስ እናንተም ሁላችሁ እንዲሁ ሚስቶቻችሁን እንደ ራሳችሁ ውደዱ፥ ሴትም ባልዋን ትፍራው።