የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መክብብ 10

10
1የሞቱ ዝንቦች ተቀምሞ የተሠራውን የዘይት ሽቶ ሊያገሙት ይችላሉ፤ እንዲሁም ትንሽ ሞኝነት ታላቅ ጥበብን ያጠፋል።
2ጥበበኛ መልካም ነገር መሥራቱ፥ ሞኝም መሳሳቱ የተለመደ ተግባር ነው። 3ሞኝ ሰው በሚተላለፍበት መንገድ ሁሉ ያለ ሐሳብ ይራመዳል፤ ለሰውም ሁሉ ሞኝነቱን ያሳውቃል።
4ጸጥ ብለህ ብትታገሥ ከባድ ለሆነው በደልህ እንኳ ይቅርታ ማግኘት ስለምትችል አለቃህ በተቈጣህ ጊዜ የሥራ ቦታህን አትልቀቅ፤
5በዓለም ላይ ሌላም ክፋት አይቻለሁ፤ ይኸውም ገዢዎች የሚፈጽሙት ግፍ ነው። 6ሞኞች ከፍተኛ ሥልጣን ሲያገኙ ባለጸጎች ግን ችላ ተብለው ዝቅተኛ ስፍራ ይዘዋል። 7መሳፍንት እንደ አገልጋዮች በእግራቸው ሲሄዱ፥ አገልጋዮች ግን በፈረስ ተቀምጠው ሲጓዙ አየሁ።
8ጒድጓድን የሚቈፍር ሰው ራሱ ይወድቅበታል፤ ቅጽርንም የሚያፈርስ በእባብ ይነደፋል፤ #መዝ. 7፥15፤ ምሳ. 26፥27። 9ድንጋይን የሚፈነቅል በፈነቀለው ድንጋይ ራሱ ይጐዳል፤ እንጨትን የሚፈልጥ በፈለጠው እንጨት ይቈስላል። 10የደነዘ መጥረቢያውን የማይስል ሰው ኀይሉን በከንቱ ይጨርሳል፤ ስለዚህ ጥሩ ውጤት ለማግኘት በጥበብ መሥራት ያስፈልጋል። 11እባብ ከነከሰህ በኋላ የእባብ ማፍዘዣ ድግምት ምንም አይጠቅምህም። 12ጥበበኛ ሰው በንግግሩ ክብርን ያገኛል፤ ሞኝ ግን በገዛ ንግግሩ ይጠፋል፤ 13የሞኝ ሰው ንግግር በሞኝነት ተጀምሮ በከባድ እብደት ይደመደማል። 14ሞኝ ሰው ልፍለፋ ያበዛል።
ወደፊት የሚሆነውን የሚያውቅ የለም፤ ሰው ከሞተ በኋላ የሚሆነውን ነገር የሚያስረዳው የለም።
15ዕውቀት የጐደለው ሞኝ ሰው ወደ ከተማ መውጣት ስለሚሳነው በሥራው ይደክማል።
16ሕፃን የሆነ ንጉሥና እየደገሱ ገና በማለዳ የሚሰክሩ መሳፍንት ያሉአት አገር ወዮላት 17በጨዋነት ያደገ ንጉሥና ለስካር ሳይሆን ብርታትና ኀይል ለማግኘት ብቻ በተወሰነ ጊዜ የሚበሉና የሚጠጡ መሪዎች ያሉአት አገር የተባረከች ናት።
18ሰው ቤቱን ከመጠገን ቸል ቢል ጣራው ይዘብጣል፤ ክዳኑም ያፈሳል።
19በምግብና በወይን ጠጅ ተድላ ደስታ ይገኛል፤ ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ ያለ ገንዘብ አይገኝም።
20የሚሰማብኝ የለም ብለህ በስውር እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትማ፤ በተኛህበት አልጋህ ላይ ሆነህም ባለጸጋን አትስደብ፤ ምሥጢርህን የሰሙ ነገር ጠላፊዎች ክንፍ እንዳለው ወፍ በረው ሊነግሩብህ ይችላሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ