በዚያን ጊዜ አንዳንድ የባቢሎን ጠቢባን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ። ንጉሡን ናቡከደነፆርንም እንዲህ አሉት፦ “ንጉሥ ሆይ! ለዘለዓለም ኑር! ንጉሥ ሆይ! አንተ የመለከት፥ የእንቢልታ፥ የመሰንቆ፥ የክራር፥ የበገናና የዋሽንት፥ የሙዚቃ ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ማናቸውም ሰው በመሬት ላይ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል እንዲሰግድ ዐዋጅ አውጥተህ ነበር። በመሬት ላይ ተደፍቶ የማይሰግድ ሰው ቢኖር በሚነደው የእሳት ነበልባል ውስጥ እንዲጣል ትእዛዝ ሰጥተሃል። እነሆ፥ በባቢሎን አውራጃዎች ላይ ገዢዎች አድርገህ የሾምካቸው ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብደናጎ የተባሉ የአይሁድ ወገኖች የአንተን ትእዛዝ አይፈጽሙም፤ አማልክትህን አያመልኩም፤ ላቆምከውም ምስል አይሰግዱም።” ንጉሡ ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጥቶ ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብደናጎ እንዲጠሩ አዘዘ፤ እነርሱም መጥተው በንጉሡ ፊት ቀረቡ። ናቡከደነፆርም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብደናጎ! አማልክቴን አለማምለካችሁና ላቆምኩትም የወርቅ ምስል አለመስገዳችሁ እርግጥ ነውን? እንግዲህ የመለከት፥ የእንቢልታ፥ የመሰንቆ፥ የክራር፥ የበገና፥ የዋሽንትና፥ የሙዚቃም ሁሉ ድምፅ ስትሰሙ ላቆምኩት ምስል በመሬት ላይ ተደፍታችሁ ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በሚነደው የእሳት ነበልባል ጒድጓድ ውስጥ ወዲያውኑ ትጣላላችሁ፤ ከእጄም የሚያድናችሁ አምላክ እንደሌለ ዕወቁ።” ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብደናጎም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ንጉሥ ሆይ! በዚህ ጉዳይ ላይ ራሳችንን የምንከላከልበት መልስ ልንሰጥህ አያስፈልገንም። እኛ የምናገለግለው አምላክ ከዚህ ከሚነደው ከእሳት ነበልባልም ሆነ ከአንተ እጅ ሊያድነን ይችላል፤ ንጉሥ ሆይ! እርሱ ሊያድነን ፈቃዱ ባይሆን እንኳ አማልክትህን እንደማናመልክና ላቆምከውም የወርቅ ምስል እንደማንሰግድ ዕወቅ።”
ትንቢተ ዳንኤል 3 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ዳንኤል 3:8-18
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos