“እግዚአብሔር ለአብርሃም በመሐላ የሰጠው ተስፋ የሚፈጸምበት ጊዜ ሲቃረብ በግብጽ የነበረው የሕዝባችን ቊጥር እየበዛ ሄደ። ይህም የሆነው ዮሴፍን የማያውቅ ሌላ ንጉሥ በግብጽ እስከ ነገሠበት ጊዜ ድረስ ነው። አዲሱ ንጉሥ በሕዝባችን ላይ በተንኰል ተነሥቶ አባቶቻችንን ይጨቊናቸው ጀመር፤ ሕፃኖቻቸውም እንዲሞቱና ወደ ውጪ አውጥተው እንዲጥሉአቸው፥ አባቶቻችንን አስገደዳቸው። በዚያን ጊዜ ሙሴ ተወለደ፤ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ያማረ ሕፃን ነበር፤ ሦስት ወር በአባቱ ቤት አደገ፤ ወደ ውጪም በተጣለ ጊዜ የፈርዖን ሴት ልጅ አነሣችውና እንደ ልጅዋ አድርጋ አሳደገችው። ሙሴም የግብጻውያንን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ። “ሙሴ አርባ ዓመት በሞላው ጊዜ ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ለመጐብኘት ተነሣሣ። ከወንድሞቹም አንዱ በአንድ ግብጻዊ ሰው ሲበደልና ሲገፋ አይቶ ረዳው፤ ለተገፋውም በመበቀል ግብጻዊውን መታና ገደለው። እግዚአብሔር በእርሱ አማካይነት ነጻ እንደሚያወጣቸው ወገኖቹ የሚገነዘቡ መስሎት ነበር፤ እነርሱ ግን ይህን አልተገነዘቡም። በማግስቱም ሁለት እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኘና ሊገላግላቸው በመፈለግ ‘እናንተ ሰዎች፥ እናንተ ወንድማማች ናችሁ፤ ስለምን ትጣላላችሁ?’ አላቸው። ያ ባልንጀራውን ይደበድብ የነበረው ሰው ሙሴን ወዲያ ገፈተረና ‘አንተን በእኛ ላይ ገዢና ፈራጅ ያደረገህ ማን ነው? ትናንትና ግብጻዊውን እንደ ገደልከው እኔንም ልትገድለኝ ትፈልጋለህን?’ አለው። ሙሴ ይህን በሰማ ጊዜ ከግብጽ አገር ሸሽቶ ወደ ምድያም አገር ሄደና እዚያ በስደት ኖረ፤ በዚያ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ።
የሐዋርያት ሥራ 7 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሐዋርያት ሥራ 7:17-29
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos