እስጢፋኖስ በጸጋና በኀይል ተሞልቶ ድንቅ ነገሮችንና ታላላቅ ተአምራትን በሕዝቡ መካከል ያደርግ ነበር፤ በዚያን ጊዜ “የነጻ ወጪዎች ምኵራብ” ከተባለው የአይሁድ ጸሎት ቤት ሰዎች፥ ከቀሬናና ከእስክንድርያ ሰዎች፥ ከኪልቅያና ከእስያ አንዳንድ ሰዎች ተነሥተው እስጢፋኖስን በመቃወም ይከራከሩት ነበር። ነገር ግን እስጢፋኖስ ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም። በዚያን ጊዜ “ይህ ሰው በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ሲናገር ሰምተነዋል” የሚሉ ሰዎችን በስውር አነሣሡበት። በዚሁ ዐይነት ሕዝቡንና ሽማግሌዎቹን የሕግ መምህራንንም በእርሱ ላይ አነሣሡ፤ ወደ እስጢፋኖስም ሄዱና ይዘው በሸንጎው ፊት አቀረቡት። በእርሱ ላይ በሐሰት የሚመሰክሩ አንዳንድ ሰዎችንም አመጡ፤ የሐሰት ምስክሮችም እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው በዚህ ቤተ መቅደስና በሕግ ላይ የስድብ ቃል ከመናገር አይቈጠብም። ደግሞም ‘ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ቤተ መቅደስ ያፈርሳል፤ ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል’ ብሎ ሲናገር ሰምተነዋል።” በዚህ ጊዜ በሸንጎው የተገኙት ሁሉ እስጢፋኖስን ትኲር ብለው ሲመለከቱት ፊቱ እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ታያቸው።
የሐዋርያት ሥራ 6 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሐዋርያት ሥራ 6:8-15
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች