በዚህ ጊዜ እስጢፋኖስ ጸጋንና ኀይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅ ነገሮችንና ታምራዊ ምልክቶችን ያደርግ ነበር። “የነጻ ወጪዎች ምኵራብ” ተብሎ የሚጠራው ምኵራብ አባላት የሆኑ ከቀሬናና ከእስክንድርያ፣ እንዲሁም ከኪልቅያና ከእስያ አውራጃዎች የመጡ ሰዎችም ተቃውሞ አስነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ጀመር፤ ይሁን እንጂ ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም። ስለዚህ፣ “እስጢፋኖስ በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ሲሰነዝር ሰምተናል” የሚሉ ሰዎችን በስውር አዘጋጁ። በዚህ ሁኔታ ሕዝቡን፣ የአገር ሽማግሌዎቹንና የሕግ መምህራኑን በማነሣሣት፣ እስጢፋኖስን አስይዘው በአይሁድ ሸንጎ ፊት አቀረቡት፤ እንዲህ ብለው የሚመሰክሩ የሐሰት ምስክሮችንም አቆሙበት፤ “ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራና በሕጉ ላይ የስድብ ቃል መናገሩን በፍጹም አልተወም፤ ምክንያቱም ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ እንደሚያጠፋና ከሙሴ የተቀበልነውን ወግ እንደሚለውጥ ሲናገር ሰምተነዋል።” በሸንጎው ተቀምጠው የነበሩትም ሁሉ እስጢፋኖስን ትኵር ብለው ሲመለከቱት ፊቱ የመልአክ ፊት መስሎ ታያቸው።
ሐዋርያት ሥራ 6 ያንብቡ
ያዳምጡ ሐዋርያት ሥራ 6
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሐዋርያት ሥራ 6:8-15
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos