የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐዋርያት ሥራ 5:17-26

የሐዋርያት ሥራ 5:17-26 አማ05

የካህናት አለቃውና ከእርሱ ጋር የነበሩት የሰዱቃውያን ወገኖች ሁሉ በቅንነት ተሞልተው በእነርሱ ላይ ተነሡ፤ ሐዋርያትን ያዙና በሕዝቡ ወህኒ ቤት አስገቡአቸው። የእግዚአብሔር መልአክ ግን በሌሊት የወህኒ ቤቱን በሮች ከፍቶ፥ አስወጣቸውና፥ “ሂዱ! በቤተ መቅደስ ቆማችሁ የዚህን ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝቡ ንገሩ!” አላቸው፤ ሐዋርያቱም ትእዛዙን ተቀብለው በማለዳ ወደ ቤተ መቅደስ ገቡና ማስተማር ጀመሩ። በዚያን ጊዜ የካህናት አለቃውና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጥተው የሸንጎውን አባሎችና የአይሁድ ሽማግሌዎችን ሁሉ በአንድነት ሰበሰቡ፤ ሐዋርያትንም እንዲያመጡአቸው ሰዎችን ወደ ወህኒ ቤት ላኩ። የዘብ ኀላፊዎቹ ግን ወደ ወህኒ ቤት ሄደው ሐዋርያትን በዚያ አላገኙአቸውም፤ ተመልሰውም መጡና “የወህኒ ቤቱ በር በጥብቅ ተቈልፎ ጠባቂዎችም በበሩ ፊት ቆመው አገኘናቸው፤ የወህኒ ቤቱን በር በከፈትነው ጊዜ ግን በውስጥ ማንንም አላገኘንም” ብለው ተናገሩ። የቤተ መቅደሱ የዘብ አዛዥና የካህናት አለቆች ይህን በሰሙ ጊዜ “ይህ ነገር ምን ይሆን?” በማለት ግራ ተጋቡ። በዚህ ጊዜ አንድ ሰው መጣና “በወህኒ ቤት ያስገባችኋቸው ሰዎች እነሆ፥ በቤተ መቅደስ ቆመው ሕዝቡን ያስተምራሉ” ብሎ ነገራቸው። ወዲያውኑ የቤተ መቅደሱ የዘበኞች አለቃና ሎሌዎቹ ሄደው አመጡአቸው፤ ያመጡአቸውም በኀይል ሳይሆን በማግባባት ነው፤ ይህንንም ያደረጉት ሕዝቡ በድንጋይ እንዳይወግራቸው በመፍራት ነው።