የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐዋርያት ሥራ 20:1-6

የሐዋርያት ሥራ 20:1-6 አማ05

ሁከቱ ጸጥ ካለ በኋላ ጳውሎስ ምእመናኑን በአንድነት አስጠርቶ በምክር ቃል አጽናናቸው፤ ተሰናብቶአቸውም ወደ መቄዶንያ ሄደ። በእነዚያ በሚያልፍባቸው ስፍራዎች ምእመናንን በብዙ ምክር እያበረታታ ወደ ግሪክ አገር ሄደ። እዚያም ሦስት ወር ቈየ፤ ከዚህ በኋላ በመርከብ ወደ ሶርያ ለመሄድ አሰበ፤ ግን አይሁድ በእርሱ ላይ ሤራ ማድረጋቸውን ባወቀ ጊዜ በመቄዶንያ በኩል ለመመለስ ወሰነ። የጲርሁስ ልጅ ሶጳጥሮስ ከቤርያ፥ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ ከተሰሎንቄ፥ ጋይዮስ ከደርቤ፥ ጢሞቴዎስ፥ ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ ከእስያ አብረውት ሄዱ። እነርሱ ቀድመውን ሄደው በጢሮአዳ ቈዩን። እኛ ግን ከቂጣ በዓል በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተሳፍረን በአምስት ቀን እነርሱ ወዳሉበት ወደ ጢሮአዳ ደረስንና እዚያ ሰባት ቀን አሳለፍን።