የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሐዋርያት ሥራ 20:1-6

ሐዋርያት ሥራ 20:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ክር​ክ​ሩም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ጳው​ሎስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ጠራና አጽ​ና​ና​ቸው፤ ተሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም፤ ወጥ​ቶም ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄደ። በዚያ አው​ራ​ጃም አልፎ ሄደ፤ በቃ​ሉም ብዙ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ግሪክ ሀገር ሄደ። በዚ​ያም ሦስት ወር ተቀ​መጠ፤ ወደ ሶር​ያም በመ​ር​ከብ ለመ​ሄድ ዐስቦ ሳለ አይ​ሁድ ስለ ተማ​ከ​ሩ​በት ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሊመ​ለስ ቈረጠ። ከእ​ር​ሱም ጋር የቤ​ርያ ሀገር ሰው የሚ​ሆን ሱሲ​ጳ​ጥ​ሮስ፥ የተ​ሰ​ሎ​ን​ቄም ሰዎች አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስና ሲኮ​ን​ዱስ፥ የደ​ር​ቤኑ ሰው ጋይ​ዮ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም፥ የእ​ስያ ሰዎች የሚ​ሆኑ ቲኪ​ቆ​ስና ጥሮ​ፊ​ሞ​ስም አብ​ረ​ውት ሄዱ። እነ​ር​ሱም ቀድ​መ​ውን ሄደው በጢ​ሮ​አስ ቆዩን። እኛ ግን ከፋ​ሲካ በኋላ ከፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ተነ​ሥ​ተን በባ​ሕር ላይ ተጕ​ዘን በአ​ም​ስት ቀን ወደ ጢሮ​አስ ደረ​ስን፤ በዚ​ያም ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥን።