የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐዋርያት ሥራ 15:36-41

የሐዋርያት ሥራ 15:36-41 አማ05

ከጥቂት ቀኖች በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “ና እንመለስና ከዚህ በፊት የጌታን ቃል ባበሠርንባቸው ከተሞች ሁሉ ያሉትን ወንድሞች እንጐብኝ፤ እንዴት እንደ ሆኑም እንወቅ” አለው። በርናባስም ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ ከእነርሱ ጋር አብሮአቸው እንዲሄድ ፈለገ። ጳውሎስ ግን ይህ ሰው ከእነርሱ ጋር እንዲሄድ አልፈቀደም፤ ያልፈቀደበትም ምክንያት እሱ በጵንፍልያ ከእነርሱ ተለይቶ ስለ ቀረና ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር ስላልሄደ ነው። በዚህ ምክንያት በጳውሎስና በበርናባስ መካከል ከፍ ያለ ክርክር ተነሣና ተለያዩ፤ ስለዚህ በርናባስ ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞችም ጳውሎስን ለጌታ ጸጋ ዐደራ ከሰጡት በኋላ ሄደ። እርሱም አብያተ ክርስቲያንን እያበረታታ በሶርያና በኪልቅያ በኩል አለፈ።