ሐዋርያት ሥራ 15:36-41
ሐዋርያት ሥራ 15:36-41 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከጥቂት ቀኖች በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “ና እንመለስና ከዚህ በፊት የጌታን ቃል ባበሠርንባቸው ከተሞች ሁሉ ያሉትን ወንድሞች እንጐብኝ፤ እንዴት እንደ ሆኑም እንወቅ” አለው። በርናባስም ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ ከእነርሱ ጋር አብሮአቸው እንዲሄድ ፈለገ። ጳውሎስ ግን ይህ ሰው ከእነርሱ ጋር እንዲሄድ አልፈቀደም፤ ያልፈቀደበትም ምክንያት እሱ በጵንፍልያ ከእነርሱ ተለይቶ ስለ ቀረና ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር ስላልሄደ ነው። በዚህ ምክንያት በጳውሎስና በበርናባስ መካከል ከፍ ያለ ክርክር ተነሣና ተለያዩ፤ ስለዚህ በርናባስ ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞችም ጳውሎስን ለጌታ ጸጋ ዐደራ ከሰጡት በኋላ ሄደ። እርሱም አብያተ ክርስቲያንን እያበረታታ በሶርያና በኪልቅያ በኩል አለፈ።
ሐዋርያት ሥራ 15:36-41 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከጥቂት ቀን በኋላም ጳውሎስ በርናባስን፦“እንግዲህስ እንመለስና የእግዚአብሔርን ቃል ባስተማርንባቸው ሀገሮች ያሉትን ወንድሞች እንጐብኛቸው፤ እንዴት እንዳሉም እንወቅ” አለው። በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ከእነርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ። ጳውሎስ ግን ከእነርሱ ጋር ሊወስደው አልፈቀደም፤ እነርሱ በጵንፍልያ ሳሉ ትቶአቸው ሄዶአልና፤ አብሮአቸውም ለሥራ አልመጣም ነበርና። ስለዚህም ተኰራርፈው እርስ በርሳቸው ተለያዩ፤ በርናባስም ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ ሄደ። በሶርያና በኪልቅያም እየዞረ አብያተ ክርስቲያናትን አጽናና።
ሐዋርያት ሥራ 15:36-41 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ጳውሎስ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በርናባስን፣ “ተነሣና የጌታን ቃል ወደ ሰበክንባቸው ከተሞች ሁሉ እንሂድ፤ በዚያ ያሉ ወንድሞችም በምን ሁኔታ እንዳሉ ለማወቅ እንጐብኛቸው” አለው። በርናባስም ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ ዐብሯቸው እንዲሄድ ፈለገ፤ ጳውሎስ ግን እርሱን ይዞ ለመሄድ አልፈለገም፤ ምክንያቱም፣ ቀደም ሲል ማርቆስ ከእነርሱ ተለይቶ በጵንፍልያ ስለ ቀረ እና ወደ ሥራ ዐብሯቸው ስላልሄደ ነበር። እንዲህ የከረረ አለመግባባት በመካከላቸው ስለ ተፈጠረ እርስ በርስ ተለያዩ፤ ስለዚህ በርናባስ ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞችም ለጌታ ጸጋ ዐደራ ከሰጡት በኋላ ተለይቷቸው ሄደ፤ አብያተ ክርስቲያናትንም እያበረታታ በሶርያና በኪልቅያ በኩል ዐለፈ።
ሐዋርያት ሥራ 15:36-41 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን፦ “ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ ወንድሞችን እንጐብኛቸው፥ እንዴት እንዳሉም እንወቅ” አለው። በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይወስድ ዘንድ አሰበ፤ ጳውሎስ ግን ይህን ከእነርሱ ጋር ሊወስድ አልፈቀደም፥ ከእነርሱ ዘንድ ከጵንፍልያ ተለይቶ ነበርና፥ ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር አልመጣም ነበርና። ስለዚህም እርስ በርሳቸው እስኪአያዩ ድረስ መከፋፋት ሆነ፥ በርናባስም ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፥ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ ወጣ፤ አብያተ ክርስትያናትንም እያጸና በሶርያና በኪልቅያ ይዞር ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 15:36-41 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ ወንድሞችን እንጐብኛቸው፤ እንዴት እንዳሉም እንወቅ፤” አለው። በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይወስድ ዘንድ አሰበ፤ ጳውሎስ ግን ይህን ከእነርሱ ጋር ሊወስድ አልፈቀደም፤ ከእነርሱ ዘንድ ከጵንፍልያ ተለይቶ ነበርና፤ ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር አልመጣም ነበርና። ስለዚህም እርስ በርሳቸው እስኪለያዩ ድረስ መከፋፋት ሆነ፥ በርናባስም ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ ወጣ፤ አብያተ ክርስትያናትንም እያጸና በሶርያና በኪልቅያ ይዞር ነበር።