2 ወደ ጢሞቴዎስ 4:9-13

2 ወደ ጢሞቴዎስ 4:9-13 አማ05

በፍጥነት ወደ እኔ እንድትመጣ ይሁን፤ ዴማስ ይህን ዓለም ወዶ ተለይቶኛል፤ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስ ወደ ገላትያ፥ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል። ከእኔ ጋር ያለው ሉቃስ ብቻ ነው፤ ማርቆስ ለአገልግሎት ስለሚጠቅመኝ ፈልገህ ይዘኸው ና። ቲኪቆስን ወደ ኤፌሶን ልኬዋለሁ። ስትመጣ በጢሮአዳ በካርፑስ ዘንድ የተውኩትን ካባ ይዘህልኝ ና፤ መጻሕፍቱንም ይልቁንም የብራና መጻሕፍቱን አምጣልኝ።