2 ጢሞቴዎስ 4:9-13

2 ጢሞቴዎስ 4:9-13 NASV

በቶሎ ወደ እኔ ለመምጣት የተቻለህን ሁሉ አድርግ፤ ዴማስ ይህን ዓለም ወድዶ፣ ትቶኝ ወደ ተሰሎንቄ ሄዷልና። ቄርቂስ ወደ ገላትያ፣ ቲቶ ወደ ድልማጥያ ሄደዋል፤ ከእኔ ጋራ ያለው ሉቃስ ብቻ ነው። ማርቆስ በአገልግሎቴ ስለሚረዳኝ ከአንተ ጋራ ይዘኸው ና። ቲኪቆስን ወደ ኤፌሶን ልኬዋለሁ። ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖስ፣ ጥቅልል መጻሕፍቱን፣ በተለይም የብራና መጻሕፍቱን አምጣልኝ።