የሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ በታመመ ጊዜ ኤልሳዕ ወደ ደማስቆ ሄደ፤ ንጉሡም የኤልሳዕን መምጣት ሰማ፤ ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች አንዱ የሆነውን አዛሄልን ጠርቶ፥ “ለነቢዩ ስጦታ ይዘህ ሂድና እኔ ከዚህ በሽታ እድን ወይም አልድን እንደ ሆነ እግዚአብሔርን እንዲጠይቅልኝ ለምነው” አለው። ስለዚህም አዛሄል በደማስቆ ከሚገኘው ምርጥ የምድር በረከት ሁሉ በአርባ ግመሎች ጭኖ ወደ ኤልሳዕ ሄደ፤ አዛሄልም ኤልሳዕን ባገኘው ጊዜ “ልጅህ ንጉሥ ቤንሀዳድ ከሕመሙ ይድን ወይም አይድን እንደ ሆነ እንድትነግረው እጠይቅህ ዘንድ ልኮኛል” አለው። ኤልሳዕም “ቤንሀዳድ እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጦልኛል፤ አንተ ግን ትድናለህ ብለህ ንገረው” አለው፤ ከዚህ በኋላ ኤልሳዕ ፊቱን በማጥቈር በሚያስፈራ ሁኔታ አዛሄልን ተመለከተው፤ ከዚህም የተነሣ አዛሄል ተጨነቀ፤ ወዲያውም ኤልሳዕ እንባውን ማፍሰስ ጀመረ፤ አዛሄልም “ጌታዬ ስለምን ታለቅሳለህ?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም “በእስራኤል ሕዝብ ላይ የምትፈጽመውን አሠቃቂ ነገር ስለማውቅ ነው፤ ምሽጎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ምርጥ የሆኑ ወጣቶቻቸውን ታርዳለህ፤ ሕፃናታቸውን በድንጋይ ላይ ትፈጠፍጣለህ፤ እርጉዞች የሆኑ ሴቶቻቸውንም ሆድ ትሰነጥቃለህ” ሲል መለሰለት። አዛሄልም “እኔ ለምንም የማልጠቅም ኢምንት ነኝ! ታዲያ ይህን ሁሉ ለማድረግ የሚያስችለውን ኀይል ከቶ ከየት አገኛለሁ?” ሲል ጠየቀ። ኤልሳዕም “አንተ የሶርያ ንጉሥ እንደምትሆን እግዚአብሔር ገልጦልኛል” ሲል መለሰለት።
ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 8 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 8:7-13
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች