የነቢያት ጉባኤ አባል የነበረ ባልዋ የሞተባት አንዲት ሴት ወደ ኤልሳዕ መጥታ “ጌታዬ ሆይ! ባሌ ሞቶብኛል! እርሱም አንተ እንደምታውቀው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ለባሌ ገንዘብ አበድሮት የነበረ አንድ ሰው በባሌ ዕዳ ፈንታ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ወስዶ ባሪያ አድርጎ ሊገዛቸው ፈልጎአል” አለችው። ኤልሳዕም “ታዲያ ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ? በቤትሽም ምን እንዳለሽ ንገሪኝ” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “በትንሽ ማሰሮ ከሚገኝ የወይራ ዘይት በቀር ሌላ ምንም የለኝም” ስትል መለሰች። ኤልሳዕም እንዲህ አላት፦ “ወደ ጐረቤቶችሽ ሄደሽ ማግኘት የምትችዪውን ያኽል ባዶ ማድጋ ለምኚ፤ ከዚህም በኋላ አንቺና ልጆችሽ ወደ ቤት ገብታችሁ መዝጊያውን ዝጉ፤ የማሰሮውንም ዘይት ወደ ማድጋዎቹ ማንቈርቈር ጀምሩ፤ እያንዳንዱ ማድጋ በሚሞላበት ጊዜ ለብቻው በማግለል አኑሩት።” ስለዚህም ሴትዮዋ ወደ ቤትዋ ሄዳ ከልጆችዋ ጋር በሩን ዘጋች፤ ዘይት የነበረበትን ትንሽ ማሰሮ አንሥታ ልጆችዋ እያቀረቡላት በማንቈርቈር በየማድጋዎቹ ሞላች። ማድጋዎቹንም ሁሉ ከሞሉ በኋላ “ሌላ ትርፍ የለም ወይ?” ስትል ጠየቀች፤ ከልጆችዋም አንዱ “ሌላ ማድጋ የለም” ሲል መለሰላት። ከዚያም በኋላ ዘይቱ መውረዱን አቆመ፤ እርስዋም ተመልሳ ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ ሄደች፤ እርሱም “እንግዲህ ዘይቱን ሸጠሽ ዕዳሽን በሙሉ ክፈይ፤ ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ የሚሆንም ብዙ ገንዘብ ይተርፍሻል” አላት።
ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 4:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos