ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 13:20-21

ሁለተኛ መጽሐፈ ነገሥት 13:20-21 አማ05

ኤልሳዕም ሞተ፤ ተቀበረም። ከሞአብ የሚመጡ አደጋ ጣዮች በየዓመቱ የእስራኤልን ምድር ይወሩ ነበር። አንድ ጊዜ የአንድ ሰው ሥርዓተ ቀብር በሚፈጽምበት ሰዓት ከእነዚያ አደጋ ጣዮች መካከል አንድ ቡድን ሲመጣ ስለ ታየ፥ የሚቀበረውን ሬሳ ወደ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ በችኰላ በመወርወር ጥለውት ሸሹ፤ ያም ሬሳ ከኤልሳዕ አስከሬን ጋር በተገናኘበት ቅጽበት ወዲያውኑ ከሞት ተነሥቶ ቆመ።