እንደገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት ለእናንተ ወይም ከእናንተ የድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆን? ሰው ሁሉ የሚያውቃችሁና የሚያነባችሁ በልባችን የተጻፋችሁ የድጋፍ ደብዳቤዎቻችን እናንተ ናችሁ። እናንተስ በእኛ አገልግሎት የመጣችሁ የክርስቶስ መልእክት መሆናችሁ ግልጥ ነው፤ ይህም መልእክት የተጻፈው በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፤ እንዲሁም በሰው ልብ ጽላት ላይ እንጂ በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፈ አይደለም። ይህን የምንልበት ምክንያት በክርስቶስ አማካይነት በእግዚአብሔር ላይ እምነት ስላለን ነው። አገልግሎታችንን መፈጸም እንድንችል ብቁ የሚያደርገን እግዚአብሔር ነው እንጂ እኛስ በገዛ ራሳችን ምንም ለማድረግ ብቁ አይደለንም። የሐዲስ ኪዳኑ አገልጋዮች እንድንሆን ብቃትን የሰጠን እርሱ ነው፤ ይህም በፊደል በተጻፈው ሕግ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ርዳታ ነው፤ በፊደል የተጻፈው ሕግ ሞትን ያመጣል፤ መንፈስ ቅዱስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos