እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎቹ ለእናንተ ወይም ከእናንተ የተጻፈ የምስጋና ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆንን? እናንተ እኮ ሰው ሁሉ የሚያውቃችሁና የሚያነብባችሁ በልባችን ላይ የተጻፋችሁ ደብዳቤዎቻችን ናችሁ፤ እናንተ በቀለም ሳይሆን በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ፣ በድንጋይ ጽላት ላይ ሳይሆን በሰው ልብ ጽላት ላይ የተጻፋችሁና በእኛ የተገለገላችሁ የክርስቶስ ግልጽ ደብዳቤ ናችሁ። በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት ይህን የመሰለ ነው፤ ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፣ በራሳችን ብቃት ከእኛ ነው የምንለው አንዳች ነገር የለንም። እርሱም በፊደል ላይ ሳይሆን በመንፈስ ላይ የተመሠረተውን የአዲሱ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን ብቁዎች አደረገን፤ ምክንያቱም ፊደል ይገድላል፤ መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።
2 ቆሮንቶስ 3 ያንብቡ
ያዳምጡ 2 ቆሮንቶስ 3
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 2 ቆሮንቶስ 3:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos