ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል መግቢያ
መግቢያ
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ክፍል ሁለት የሚጀምረው መጽሐፈ ዜና መዋዕል ክፍል አንድ ካቆመበት ስፍራ ነው። ይኸውም በንጉሥ ሰሎሞን አገዛዝ ይጀምርና እስከ ሞቱ ይዘልቃል፤ በኢዮርብዓም መሪነት በሰሜን ያሉት ነገዶች በአባቱ በሰሎሞን እግር ተተክቶ በነገሠው የይሁዳ ንጉሥ ሮብዓም ላይ የማመፃቸውን ሁኔታ ከተረከ በኋላ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ፈረሰችበት ከክርስቶስ ልደት በፊት እስከ አምስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ዓመት ድረስ ያለውን የደቡባዊውን የይሁዳን መንግሥት ታሪክ አጠቃሎ ይዘረዝራል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የሰሎሞን ጥበብና ሀብት (1፥1-17)
የቤተ መቅደስ መሠራትና መመረቅ (2፥1—7፥22)
በሰሎሞን ዘመን የተፈጸሙ ሌሎች ጉዳዮች (8፥1—9፥28)
የሰሎሞን ሞት (9፥29-31)
የእስራኤል ሰሜናዊ ነገዶች በንጉሥ ሮብዓም ላይ ማመፅ (10፥1-19)
የይሁዳ ነገሥታት (11፥1—28፥27)
ንጉሥ ሕዝቅያስና የአሦራውያን ወረራ (29፥1—32፥33)
ንጉሥ ምናሴና ንጉሥ አሞን (33፥1-25)
ንጉሥ ኢዮስያስና የእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ (34፥1—35፥27)
የመጨረሻዎቹ የይሁዳ ነገሥታት (36፥1-16)
የኢየሩሳሌም መፍረስና የሕዝብዋ ወደ ባቢሎን መወሰድ (36፥17-21)
የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ አይሁድ ወደ ይሁዳ እንዲመለሱ መፍቀዱ (36፥22-23)
Currently Selected:
ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997