የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 27

27
የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአታም
(2ነገ. 15፥32-38)
1ኢዮአታም ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ሲሆነው ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ይሩሻ ተብላ የምትጠራ የሳዶቅ ልጅ ነበረች። 2ኢዮአታም አባቱ እንዳደረገው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር ሠራ፤ አባቱ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ዕጣን በማጠን ያደረገውን ኃጢአትም አልሠራም፤ ሕዝቡ ግን ኃጢአት መሥራቱን ቀጥሎ ነበር።
3ኢዮአታም የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ በር እንደገና ሠራ፤ በተጨማሪም በኢየሩሳሌም በሚገኘው ዖፌል ተብሎ በሚጠራው ኰረብታማ ቦታ የከተማ ቅጽሮችን በመሥራት ብዙ ሥራ አከናውኖአል፤ 4እንዲሁም በይሁዳ ተራራማ ስፍራዎች ላይ ከተሞችን፥ ደን በበዛባቸው ስፍራዎችም ላይ ምሽጎችንና ቅጽሮችን ሠርቶ ነበር። 5በዐሞን ንጉሥና በሠራዊቱ ላይ ጦርነት ከፍቶ ድል አድርጎአቸው ነበር፤ ዐሞናውያንንም በየዓመቱ ለሦስት ዓመት በተከታታይ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ የሚመዝን ብር፥ አንድ ሚሊዮን ኪሎ የሚመዝን ስንዴና እንዲሁም አንድ ሚሊዮን ኪሎ የሚመዝን ገብስ እንዲገብሩለት አስገደዳቸው። 6ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን ስለ አቀና ገናና እየሆነ ሄደ። 7በኢዮአታም ዘመነ መንግሥት የተፈጸመው ሌላው ድርጊት ሁሉ፥ ያካሄደው ጦርነትና የመንግሥቱ አመራር ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጻሕፍት ተመዝግበው ይገኛሉ፤ 8ኢዮአታም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ 9ከዚያም በኋላ ሞተ፤ በዳዊት ከተማም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አካዝ ነገሠ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ