1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:14-15

1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:14-15 አማ05

አንድ ግንበኛ በመሠረቱ ላይ የሠራው ሥራ በእሳት ተፈትኖ ሳይጐዳ ጸንቶ ከቆመ ግንበኛው ዋጋውን ያገኛል። ሥራው በእሳት ተቃጥሎ የተደመሰሰበት ግንበኛ ግን ዋጋው ይቀርበታል፤ ይሁን እንጂ እርሱ ራሱ፥ በእሳት ውስጥ አልፎ ሳይቃጠል እንደሚቀር ሰው ይድናል።