የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:29-34

1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:29-34 አማ05

እንግዲህ የሞቱ ሰዎች የማይነሡ ከሆነ ስለ ሞቱ ሰዎች የሚጠመቁ ሁሉ ትርፋቸው ምንድን ነው? የሞቱ ሰዎች ከቶ የማይነሡ ከሆነ ሰዎች በእነርሱ ምትክ ስለምን ይጠመቃሉ? እኛስ ብንሆን በየሰዓቱ ለአደጋ እየተጋለጥን የምንኖረው ለምንድን ነው? ወንድሞች ሆይ! እኔን በየቀኑ ሞት ያጋጥመኛል፤ ይህንንም የምነግራችሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በእናንተ ላይ ያለኝ ትምክሕት እርግጠኛ ስለ ሆነ ነው። እንደ ሰው አስተሳሰብ እኔ በኤፌሶን ከአራዊት ጋር መታገሌ ጥቅሜ ምንድን ነው? ሙታን ከሞት የማይነሡ ከሆነማ “ነገ ስለምንሞት ኑ እንብላ፤ እንጠጣ” እንደ ተባለው መሆኑ ነው። አትታለሉ፤ “መጥፎ ጓደኛ ጥሩውን ጠባይ ያበላሻል።” ወደ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአትም አትሥሩ፤ በእናንተ መካከል አንዳንዶች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉ። ይህንንም የምለው እንድታፍሩ ብዬ ነው።