የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 3

3
የንጉሥ ዳዊት ትውልድ
1-3ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ስም እንደ ዕድሜአቸው ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ነው፦
በኲሩ የኢይዝራኤል ተወላጅ ከሆነችው ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥
ሁለተኛው የቀርሜሎስ ተወላጅ ከሆነችው ከአቢጌል የተወለደው ዳንኤል፥
ሦስተኛው የገሹር ንጉሥ የታልማይ ልጅ ከሆነችው ከማዕካ የተወለደው አቤሴሎም፥
አራተኛው ከሐጊት የተወለደው አዶንያስ፥
አምስተኛው ከአቢጣል የተወለደው ሸፋጥያ፥
ስድስተኛው ከዔግላ የተወለደው ዩትረዓም፤
4እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት በኬብሮን ሲሆን ዳዊት መኖሪያውን በዚያ አድርጎ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ወቅት ነው።
ዳዊት መኖሪያውን በኢየሩሳሌም አድርጎ ሠላሳ ሦስት ዓመት ገዛ፤ #2ሳሙ. 5፥4-5፤ 1ነገ. 2፥11፤ 1ዜ.መ. 29፥27። 5በዚያም ብዙ ወንዶች ልጆችን ወለደ።
የዓሚኤል ልጅ ቤርሳቤህ ሺምዓ፥ ሾባብ፥ ናታንና ሰሎሞን ተብለው የሚጠሩ አራት ወንዶች ልጆችን ወለደችለት። #2ሳሙ. 11፥3።
6ሌሎች ዘጠኝ ወንዶች ልጆችም ነበሩት፤ እነርሱም ይብሐር፥ ኤሊሹዓ፥ ኤሊፋሌጥ፥ 7ኖጋህ፥ ኔፌግ፥ ያፊዓ፥ 8ኤሊሻማዕ፥ ኤሊያዳዕና ኤሊፌሌጥ ተብለው የሚጠሩ ናቸው፤ 9ከእነዚህም ሌላ ዳዊት ከቊባቶቹ የወለዳቸው ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ትዕማር ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅም ነበረችው።
የንጉሥ ሰሎሞን ትውልድ
10የንጉሥ ሰሎሞን የትውልድ ሐረግ ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ነው፥ ሰሎሞን፥ ሮብዓም፥ አቢያ፥ አሳ፥ ኢዮሣፍጥ፥ 11ኢዮራም፥ አካዝያስ፥ ኢዮአስ፥ 12አሜስያስ፥ ዐዛርያስ፥ ኢዮአታም፥ 13አካዝ፥ ሕዝቅያስ፥ ምናሴ፥ 14አሞንና ኢዮስያስ፤ 15የኢዮስያስም ልጆች በኲሩ ዮሐናን፥ ሁለተኛው ኢዮአቄም፥ ሦስተኛው ሴዴቅያስና አራተኛው ሻሉም ናቸው፤ 16ኢዮአቄም ደግሞ ኢኮንያንና ጼዴቅያ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ።
የንጉሥ ኢኮንያን የትውልድ ሐረግ
17-18የባቢሎን ምርኮኛ የነበረው የኢኮንያን ልጆች ሰላትያል፥ ማልኪራም፥ ፈዳያ፥ ሼናጻር፥ ይቃምያ፥ ሆሻማዕና ነዳብያ ተብለው የሚጠሩ ናቸው። 19ፈዳያም ዘሩባቤልና ሺምዒ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዘሩባቤልም መሹላምና ሐናንያ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችና ሰሎሚት ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅ ነበሩት። 20እንዲሁም ሌሎች አምስት ወንዶች ልጆች ሲኖሩት፥ እነርሱም ሐሹባ፥ ኦሔል፥ ቤሬክያ፥ ሐሳድያና ዩሻብሔሴድ ተብለው የሚጠሩ ናቸው።
21ሐናንያም ፈላጥያና ይሻዕያ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ይሻዕያም ረፋያን ወለደ፤ ረፋያም አርናንን ወለደ፤ አርናን አብድዩን ወለደ፤ አብድዩም ሸካንያን ወለደ፤ 22ሸካንያም ሸማዕያን ወለደ፤ ሸማዕያም ሐጡሽ፥ ዩጋል፥ ባሪያሕ፥ ነዓርያና ሻፋጥ ተብለው የሚጠሩትን አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ የሸካያ ትውልድ በድምሩ ስድስት ነበር፤ 23ነዓርያም ኤልዮዔናይ፥ ሕዝቅያስና ዓዝሪቃም ተብለው የሚጠሩትን ሦስት ልጆችን ወለደ፤ 24ኤልዮዔናይም ሆዳውያ፥ ኤልያሺብ፥ ፐላያ፥ ዓቁብ፥ ዮሐናን፥ ደላያና ዐናኒ ተብለው የሚጠሩትን ሰባት ወንዶች ልጆችን ወለደ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ