የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 2

2
የይሁዳ ትውልድ
1ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥ 2ዳን፥ ዮሴፍ፥ ብንያም፥ ንፍታሌም፥ ጋድና አሴር ናቸው።
3ይሁዳ ከከነዓናዊት ሚስቱ ከባትሹዓ ዔር፥ ኦናንና ሼላ ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ የበኲር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ስለ ነበር እግዚአብሔር በሞት ስለ ቀሠፈው፥ 4ይሁዳ የልጁ ሚስት ከነበረችው ከትዕማር ፋሬስና ዛራሕ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። የይሁዳ ልጆች በድምሩ አምስት ነበሩ።
5ፋሬስም ሔጽሮንና ሐሙል የተባሉ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ 6የእርሱም ወንድም ዛራሕ አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ዚምሪ፥ ኤታን፥ ሄማን፥ ካልኮልና ዳርዳዕ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ 7ከዛራሕ ትውልድ አንዱ የሆነው የካርሚ ልጅ ዓካን ለእግዚአብሔር ከተለየው ምርኮ በስርቆት ወስዶ በመደበቁ ምክንያት በእስራኤል ሕዝብ ላይ መቅሠፍት አምጥቶ ነበር። #ኢያሱ 7፥1።
8ኤታንም ዐዛርያ የተባለ አንድ ወንድ ልጅ ወለደ።
የንጉሥ ዳዊት የትውልድ ሐረግ
9ሔጽሮን ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ይራሕመኤል፥ ራምና ካሌብ ተብለው የሚጠሩ ናቸው፤ 10አራም የአሚናዳብ አባት ነበር፤ አሚናዳብም የይሁዳ ልጆች አለቃ የሆነው ነአሶንን ወለደ። 11ነአሶን ሳልሞንን ወለደ፤ ሳልሞንም ቦዔዝን ወለደ። 12ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ። 13እሴይ የበኲር ልጁን ኤሊአብንና ሁለተኛውን አሚናዳብን፥ ሦስተኛውን ሻማን፥ 14አራተኛውን ናትናኤልን አምስተኛውን ራዳይን፥ 15ስድስተኛውን ኦጼምና ሰባተኛውን ዳዊትን ወለደ። 16እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢጌል ይባሉ ነበር፤ የጽሩያም ሦስት ወንዶች ልጆች አቢሳይ፥ ኢዮአብና ዓሣሄል ተብለው ይጠሩ ነበር። 17ሌላይቱ የእሴይ ሴት ልጅ አቢጌል የእስማኤል ዘር የሆነውን ዬቴርን አግብታ ዐማሣ ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደች።
የሔጽሮን ትውልድ
18የሔጽሮን ልጅ ካሌብ ዐዙባ የተባለች ሴት አግብቶ ይሪዖት ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅ ወለደ፤ ይሪዖትም ዬሼር፥ ሾባብና አርዶን ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደች። 19ዐዙባ ከሞተችም በኋላ ካሌብ ኤፍራታ ተብላ የምትጠራ ሴት አግብቶ ሑር ተብሎ የሚጠራ ወንድ ልጅ ወለደ፤ 20ሑርም ኡሪ የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ኡሪም ባጽልኤል ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደ።
21ሔጽሮን ሥልሳ ዓመት ሲሞላው የገለዓድ እኅት የነበረችውን የማኪርን ልጅ አግብቶ ሰጉብ የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ 22ሰጉብም ያኢር ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ያኢር በገለዓድ ግዛት ውስጥ የሚገኙትን ኻያ ሦስት ከተሞች ይገዛ ነበር፤ 23ነገር ግን የገሹርና የአራም ነገሥታት ሥልሳ የሚያኽሉ ታናናሽ ከተሞችን ከዚያው ከገለዓድ ድል አድርጎ ያዘ፤ ይህም የያኢርንና የቀናትን መንደሮች እንዲሁም በአቅራቢያቸው ያሉትንም ታናናሽ ከተሞች የሚያጠቃልል ነበር፤ በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ናቸው፤ 24ከሔጽሮን በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ ሚስቱ አብያ አሽሑር የተባለውን ልጁን ወለደችለት አሽሑርም የተቆዓ አባት ነው።
የይራሕመኤል ትውልድ
25የሔጽሮን የበኲር ልጅ ይራሕመኤል አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም የመጀመሪያው ራም ቀጥሎም ቡና፥ ኦሬን፥ ኦጼምና አሒያ ተብለው የሚጠሩ ነበሩ፤ 26-27ራም ሦስት ወንድ ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ማዓጽ፥ ያሚንና ዔቄር ተብለው የሚጠሩ ናቸው፤ ይራሕመኤል፥ ዐታራ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሌላ ሴት አግብቶ ኦናም ተብሎ የሚጠራ ወንድ ልጅ ወለደ፤ 28ኦናምም ሻማይና ያዳዕ የተባሉ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ሻማይም ናዳብና አቢሹር የተባሉ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ።
29አቢሹርም አቢኃይል ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት አግብቶ አሕባንና ሞሊድ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ 30ናዳብ ሴሌድና አፋይም የተባሉ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ሴሌድ ግን አንድም ልጅ ሳይወልድ ሞተ። 31አፋይምም ዩሺዒ የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ዩሺዒም ሼሻን የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ። ሼሻንም አሕላይ የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ።
32የሻማይ ወንድም ያዳዕ ዬቴርና ዮናታን ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዬቴር ግን አንድም ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ 33ዮናታንም ፔሌትና ዛዛ የተባሉ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የይራሕመኤል ዘሮች ናቸው።
34ኤሻን ከሴቶች በቀር ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ እርሱም ያርሐዕ ተብሎ የሚጠራ አንድ ግብጻዊ አገልጋይ ነበረው፤ 35ለዚህም ለአገልጋዩ ከሴቶች ልጆቹ አንዲቱን ዳረለት፤ ያርሐዕምም ዓታይ ተብሎ የሚጠራ አንድ ወንድ ልጅ ወለደ፤ 36ከዓታይ እስከ ኤሊሻማዕ ያለው የትውልድ ሐረግ፥ ኢታይ፥ ናታን፥ ዛባድ፥ 37ኤፍላል፥ ዖቤድ፥ 38ኢዩ፥ ዐዛርያ፥ 39ሔሌጽ፥ ኤልዓሳ፥ 40ሲስማይ፥ ሻሉም፥ 41ይቃምያና ኤሊሻማዕ ነው።
ሌሎቹ የካሌብ ትውልድ
42የይራሕመኤል ወንድም የነበረው የካሌብ በኲር ልጅ ስሙ ሜሻዕ ይባል ነበር፤ ይህም ሜሻዕ ዚፍ ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ዚፍም ማሬሻን ወለደ፤ ማሬሻም ኬብሮንን ወለደ፤ 43ኬብሮንም ቆሬ፥ ታፑሐ፥ ሬቄምና ሼማዕ ተብለው የሚጠሩትን አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ። 44ሼማዕም ራሐምን ወለደ፤ ራሐምም ዮርቀዓምን ወለደ፤ የሼማዕ ወንድም ሬቄም ሻማይን ወለደ፤ 45ሻማይም ማዖንን ወለደ፤ ማዖንም ቤትጹርን ወለደ።
46ካሌብ ዔፋ ተብላ የምትጠራ ቊባት ነበረችው፤ ከእርስዋም ሐራን፥ ሞጻና ጋዜዝ ተብለው የሚጠሩ ሌሎች ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ሐራንም ጋዜዝ ተብሎ የሚጠራ ሌላም ወንድ ልጅ ወለደ።
47ያህዳይ የተባለውም ሰው ሬጌም፥ ዮታም፥ ጌሻን፥ ፔሌጥ፥ ዔፋና ሻዓፍ ተብለው የሚጠሩ ስድስት ወንዶች ልጆችን ወለደ።
48ካሌብ፥ ማዕካ የተባለች አንዲት ሌላ ቊባት ነበረችው፤ ከእርስዋም ሼቤርና ቲርሐና ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ 49ይህችው ሴት ዘግየት ብላ ሌሎች ሁለት ወንዶች ልጆችን እነርሱም የማድማናን አባት ሳፋንና የማክቢናና የጊብዓን አባት ሻዋን ወለደችለት።
ካሌብ በተጨማሪ ዓክሳ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ነበረችው።
50ከዚህ የሚከተሉትም የካሌብ ዘሮች ናቸው፦ ሑር የካሌብ ከሚስቱ ከኤፍራታ የተወለደው የመጀመሪያው ልጁ ሲሆን የሑር ልጅ የቂርያትይዓሪም አባት ሾባል ነው፤ 51የሑር ሁለተኛው ልጅ ሳልማ ደግሞ የቤተልሔም አባት፥ የሑር ሦስተኛ ልጅ ሐሬፍ የቤት ጋዴር አባት ነው።
52የቂርያትይዓሪም አባት ሾባል ሌሎችም ልጆች ነበሩት፦ እነርሱም ሔሮኤትና የመኑሖት ጐሣዎች እኩሌታ ነበሩ። 53እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ቤተሰቦች ዩትራውያን፥ ፑታውያን፥ ሹማታውያንና ሚሽራዓውያን ተብለው የሚጠሩ ነበሩ፤ ከእነርሱም የጾርዓና የኤሽታኦል ትውልድ ተገኙ።
54የሳልማ ልጆች ቤተልሔም፥ ነጦፋውያን፥ ዐጣሮት ቤት ዮአብ፥ የመናሐታውያን እኩሌታና ጾርዓውያን ነበሩ።
55ቲርዓውያን፥ ሺምዓውያንና ሱካውያን የተባሉት ታሪክ በመጻፍና በመገልበጥ ጥበበኞች የነበሩት ጐሣዎች ያዕቤጽ ተብላ በምትጠራ ትንሽ ከተማ ይኖሩ ነበር፤ እነርሱም ከሬካባውያን አባት ከሐሜት የወጡ ቄናውያን ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ