የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 4

4
የይሁዳ የትውልድ ሐረግ
1የይሁዳም ዘሮች ፋሬስ፥ ሔጽሮን፥ ካርሚ፥ ሑርና ሾባል ናቸው። 2ሾባል ረአያን ወለደ፤ ረአያም ያሐትን ወለደ፤ ያሐትም በጾርዓ ለሚኖሩት ሕዝቦች የቀድሞ አባቶች የነበሩትን አሑማይንና ላሃድን ወለደ። 3-4ሑር የካሌብና የኤፍራታ በኲር ልጅ ነው፤ ከእርሱ ልጆች መካከል በቤተልሔም የሰፈሩ አሉ፤ ሌሎቹም የሑር ልጆች ጰኑኤልና ዔዜር ናቸው፤ የኤታም ወንዶች ልጆች ኤይዝርኤል፥ ኢሻማ፥ ኤድባሽ፥ ጌዶርን የመሠረተው ፋኑኤልና ሑሻን የመሠረተው ኤጼር ሲሆኑ ሐጽሌልጶኒ የምትባል እኅት ነበረቻቸው።
5የተቆዓን ከተማ የቈረቈረው አሽሑር፥ ሔላና ናዕራ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ 6አሽሑርም ናዕራ ከተባለችው ሚስቱ አሑዛም፥ ሔፌር፥ ቴምኒና አሓሽታሪ ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ 7እንዲሁም ሔላ ከተባለችው ሚስቱ ጼሬት፥ ይጽሐርና፥ ኤትናንና ቆጽ ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ። 8ቆጽም ዓኑብና ጾቤባ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እንዲሁም ቆጽ የሃሩም ልጅ የአሐርሔል ዘሮች ለሆኑት ጐሣዎች የነገድ አባት ነው።
9ከቤተሰቡ መካከል እጅግ የተከበረ ያዕቤጽ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እናቱ እርሱን በወለደች ጊዜ ከባድ የምጥ ጣር ደርሶባት ስለ ነበር “ያዕቤጽ” የሚል ስም አወጣችለት፤ 10ያዕቤጽም “አምላኬ ሆይ፥ ባርከኝ፤ ሰፊ ምድርንም ስጠኝ፤ እጅህ ከእኔ ጋር ይሁን፤ ሥቃይ ሊያስከትልብኝ ከሚችል ከማንኛውም ክፉ ነገር ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
ሌሎች ቤተሰቦች
11የሹሐ ወንድም ከሉብ መሒር ተብሎ የሚጠራ አንድ ወንድ ልጅ ወለደ፤ መሒርም ኤሽቶንን ወለደ፤ 12ኤሽቶንም ቤትራፋ፥ ፋሴሐና ተሒና ተብለው የሚጠሩትን ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ተሒናም ናሐሽ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ቈረቈረ፤ የእነዚህም ዘሮች ሬካ ተብላ በምትጠራ አገር ይኖሩ ነበር።
13ቀናዝም ዖትኒኤልና ሠራያ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዖትኒኤልም ሐታትና መዖኖታይ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ 14መዖኖታይ ዖፍራን ወለደ።
ሠራያም የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች የሚኖሩባትን ጌሐራሺም ተብላ የምትጠራውን ከተማ የመሠረተው ኢዮአብን ወለደ፦
15የይፉኔ ልጅ ካሌብም ዒሩ፥ ኤላና ናዓም ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ኤላም ቀናዝን ወለደ።
16ይሃልኤልም ዚፍ፥ ዚፋ፥ ቲረያና አሳርኤል ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ። 17-18ዔዝራም ዬቴር፥ ሜሬድ፥ ዔፌርና ያሎን ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ። ሜሬድም ቢትያ የተባለችውን የግብጽን ንጉሥ ልጅ አግብቶ ማርያም ተብላ የምትጠራውን ሴት ልጅና ሻማይና ዩሽባሕ ተብለው የሚጠሩትን ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዩሽባሕም ኤሽተሞዓ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ቈረቈረ፤ ሜሬድም ከይሁዳ ነገድ አንዲት ሴት አግብቶ የገዶርን ከተማ የቈረቈረውን ዬሬድን፥ የሶኮን ከተማ የቈረቈረውን ሔቤርንና፥ የዛኖሐን ከተማ የቈረቈረውን የቂቲኤልን ወለደ።
19ሆድያም የናሐምን እኅት አገባ፤ የእነርሱም ዘሮች በቀዒላ ከተማ ይኖሩ ለነበሩት ለጋርሚ ጐሣዎችና በኤሽተሞዓ ከተማ ይኖሩ ለነበሩት ለማዕካት ጐሣዎች አባቶች ሆኑ።
20ሺሞንም አምኖን፥ ሪና፥ ቤንሐናንና ቲሎን ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ።
ዩሽዒም ዞሔትና ቤንዞሔት ተብለው የሚጠሩትን ወንዶች ልጆች ወለደ።
የሼላ ትውልድ
21ሼላ ከይሁዳ ወንዶች ልጆች አንዱ ሲሆን ዘሮቹም የሌካን ከተማ የቈረቈረው ዔር፥ የማሬሻን ከተማ የቈረቈረው ላዕዳ፥ የቤት አሽቤዓ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑት የበፍታ ጨርቅ ሠሪዎች ጐሣ፥ 22ዮቂምና በኮዜባ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ሞአባውያን ሴቶችን አግብተው በቤተልሔም ሰፍረው የነበሩት ኢዮአስና ሳራፍ ናቸው፤ (ይህ የቤተሰብ መዝገብ ጥንታዊ ነው፤) 23እነርሱም የቤተ መንግሥት ሸክላ ሠራተኞች ሆነው ነጣዒምና ገዴራ ተብለው በሚጠሩ ከተሞች ይኖሩ ነበር።
የስምዖን ትውልድ
24ስምዖን፥ ነሙኤል፥ ያሚን፥ ያሪብ፥ ዜራሕና ሻኡል ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ 25ሻኡልም፥ ሻሉምን ወለደ፤ ሻሉምም ሚብሳምን ወለደ፤ ሚብሳምም ሚሽማዕን ወለደ፤ 26ሚሽማዕ ሔሙኤልን፥ ሐሙኤልም ዛኩርን፥ ዛኩር ሺምዒን ወለደ፤ 27ሺምዒ፥ ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ ወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልወለዱም፤ ስለዚህም የስምዖን ነገድ የይሁዳን ነገድ ያኽል አልበዛም።
28እስከ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ድረስ የስምዖን ዘሮች በሚከተሉት ከተሞች ይኖሩ ነበር፦ ቤርሳቤህ፥ ሞላዳ፥ ሐጻርሹዓል፥ 29ቢልሃ፥ ዔጼም፥ ቶላድ፥ 30በቱኤል፥ ሖርማ፥ ጺቅላግ፥ 31ቤትማርካቦት፥ ሖጻር ሱሲም፥ ቤትቢሪና ሻዕራይም፤ 32እንዲሁም ዔጣም፥ ዓይን፥ ሪሞን፥ ቶኬንና ዐሻን ተብለው በሚጠሩ በሌሎች አምስት ታናናሽ ከተሞችና፥ 33በአካባቢያቸው በሚገኙ መንደሮች ይኖሩ ነበር፤ ይህም እነርሱ የሚኖሩበት ስፍራ እስከ ባዕላት ከተማ ይዘልቅ ነበር። እንግዲህ የስምዖን ዘሮች ስለ ቤተሰቦቻቸውና ስለሚኖሩባቸው ስፍራዎች መዝግበው ያቈዩት ጽሑፍ ይህ ነበር። #ኢያሱ 19፥2-8።
34የየጐሣ አለቆቻቸውም ከዚህ በታች የተመለከቱት ናቸው፦
መሾባብ፥ ያምሌክ፥ የአሜስያስ ልጅ ዮሻ፥
35ዮኤል፥ የዮሺብያ ልጅ ኢዩ፥ (የሠራያ ልጅ ዮሺብያ፥ የአሰኤል ልጅ ሠራያ፥)
36ኤልዮዔናይ፥ ያዕቆባ፥ የሾሐያ፥ ዐሳያ፥ ዐዲኤል፥ የሺሚኤል በናያ፥
37የሺፍዒ ልጅ ዚዛ፥ የየዳያ የሺምሪና የሸማዕያ ዘር የሆነው የአሎን ልጅ ሺፍዒ።
38የእነዚህም ቤተሰብ እየበዛ ሄደ፤ 39እስከ ገራር ድረስ ተሠራጩ፤ በሸለቆው በስተ ምሥራቅ በኩል ከተማይቱ በምትገኝበት ስፍራም በጎቻቸውን ያሰማሩ ነበር፤ 40በዚያም ጸጥታና ሰላም በሰፈነበት ገላጣማ አገር ለም የሆነ የግጦሽ ቦታ በብዛት አገኙ፤ ቀደም ሲል በዚያ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች ከካም ዘሮች ነበሩ።
41በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች ወደ ገራር ሄደው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ድንኳንና ጎጆ ሁሉ አፈራረሱ፤ የካምን ነገዶችና መዑናውያንንም ፈጽመው ፈጁአቸው ለበጎቻቸው ብዙ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም ሕዝቡን አባረው ለዘለቄታው እዚያው መኖር ጀመሩ። 42ከስምዖን ዘሮች አምስት መቶ የሚሆኑት ወደ ኤዶም ተራራ ሄዱ፤ እነርሱም ይመሩ የነበሩት በዩሽዒ ልጆች በፐላጥያ፥ በነዓርያ፥ በረፋያና በዑዚኤል ነበር፤ 43እነርሱም በዚያ ቀርተው የነበሩትን ዐማሌቃውያንን ፈጁ፤ ከዚያን ጊዜም አንሥቶ በዚያ መኖር ጀመሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ