አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 25

25
የቤተ መቅደስ መዘምራን
1ንጉሥ ዳዊትና የሌዋውያን አለቆች የአሳፍን፥ የሔማንና የይዱቱን ልጆች መንፈስ ቅዱስ ያቀበላቸውን መዝሙር በመሰንቆ፥ በበገናና በጸናጽል እየታጀቡ እንዲዘምሩ ለዩአቸው። ለዚህ አገልግሎት የተመደቡት ሰዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦
2ዛኩር፥ ዮሴፍ፥ ነታንያና አሳርኤላ ተብለው የሚጠሩት አራቱ የአሳፍ ልጆች ሲሆኑ፥ ንጉሡ ትእዛዝ ባስተላለፈ ቊጥር የእግዚአብሔር መንፈስ ያቀበለውን መዝሙር የሚያሰማው አሳፍ የእነርሱ መሪ ነበር።
3ገዳልያ፥ ጸሪ፥ ያሻያ፥ ሺምዒ፥ ሐሻብያና ማቲትያ ተብለው የሚጠሩት ስድስቱ የይዱቱን ልጆች ሲሆኑ እነርሱም በበገና ድምፅ እየታጀቡ በአባታቸው መሪነት የእግዚአብሔር መንፈስ ያቀበላቸውን መዝሙር እያሰሙ እግዚአብሔርን በዝማሬ ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።
4ቀጥሎም ዐሥራ አራቱ የሄማን ልጆች ሲሆኑ እነርሱም ቡቂያ፥ ማታንያ፥ ዑዚኤል፥ ሸቡኤል፥ ያሪሞት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤሊአታ፥ ጊዳልቲ፥ ሮማምቲዔዜር፥ ዮሽበቃሻ፥ ማሎቲ፥ ሆቲርና ማሕዚአት ናቸው፤ 5እግዚአብሔር የንጉሡ ነቢይ ለሆነው ለሄማን እነዚህን ዐሥራ አራት ወንዶች ልጆችና ሦስት ሴቶች ልጆችን ጭምር ሰጠው፤ ይህንንም ያደረገው የሄማንን ኀይል ከፍ ለማድረግ ቀደም ሲል በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው። 6ወንዶች ልጆቹ ሁሉ በቤተ መቅደስ የሚካሄደውን የአምልኮ ሥነ ሥርዓት በማጀብ በአባታቸው መሪነት ጸናጽል ያንሿሹና መሰንቆና በገና ይደረድሩ ነበር፤ አሳፍ፥ ይዱታንና ሄማን በንጉሡ ሥልጣን ሥር ነበሩ።
7ከእነርሱም ጋር ለእግዚአብሔር አገልግሎት በዜማ መሣሪያ ያሠለጠኑ ዘመዶቻቸው ነበሩ፤ እነርሱም ሁለት መቶ ሰማኒያ ስምንት ነበሩ።
8የሥራ ምድባቸውን ለመወሰን ወጣት ሆነ ሽማግሌ፥ አስተማሪም ሆነ ተማሪ ለማንም ልዩነት ሳይደረግ ዕጣ ይጣጣሉ ነበር።
9-31የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለዮሴፍ ወጣ፤ እርሱም፥ ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤
ሁለተኛው ለገዳልያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
ሦስተኛ ለዛኩር ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
አራተኛው ለይጽሪ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፥
አምስተኛ ለነታንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤
ስድስተኛ ለቡቅያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤
ሰባተኛ ለአሳርኤላ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤
ስምንተኛው ለያሻዕያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤
ዘጠነኛው ለማታንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
ዐሥረኛው ለሺምዒ ወጣ፤ እርሱም፥ ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤
ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤
ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሻብያ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
ዐሥራ ሦስተኛው ለሹባኤል ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
ዐሥራ አራተኛ ለማቲትያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤
ዐሥራ አምስተኛው ለያሪሞት ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤
ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤
ዐሥራ ሰባተኛው ለዮሽበቃሽ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤
ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤
ዐሥራ ዘጠነኛ ለማሎቲ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
ኻያኛ ለኤሊአታ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
ኻያ አንደኛ ለሆቲር ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
ኻያ ሁለተኛ ለጊደልቲ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
ኻያ ሦስተኛ ለማሕዚኦት ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
ኻያ አራተኛ ለሮሚምቲዔዜር ወጣ፤ እርሱም ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ