አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 2:1-4

አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 2:1-4 አማ05

ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥ ዳን፥ ዮሴፍ፥ ብንያም፥ ንፍታሌም፥ ጋድና አሴር ናቸው። ይሁዳ ከከነዓናዊት ሚስቱ ከባትሹዓ ዔር፥ ኦናንና ሼላ ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ የበኲር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ስለ ነበር እግዚአብሔር በሞት ስለ ቀሠፈው፥ ይሁዳ የልጁ ሚስት ከነበረችው ከትዕማር ፋሬስና ዛራሕ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። የይሁዳ ልጆች በድምሩ አምስት ነበሩ።