የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 1

1
ከአዳም እስከ አብርሃም ያለው የትውልድ ሐረግ
(ዘፍ. 5፥1-3210፥1-3211፥10-26)
1አዳም ሤትን ወለደ፤ ሤት ሄኖስን ወለደ፤ ሄኖስ ቃይናንን ወለደ፤ 2ቃይናን መሀላልኤልን ወለደ፤ መሀላልኤል ያሬድን ወለደ፤ እነርሱም በየስማቸው ለሚጠሩ ሕዝቦች የቀድሞ አባቶች ናቸው። 3ያሬድ ሔኖክን ወለደ፤ ሔኖክ ማቱሳላን ወለደ፤ ማቱሳላ ላሜሕን ወለደ፤ 4ላሜሕ ኖኅን ወለደ፤ ኖኅ ሴምን፥ ካምንና ያፌትን ወለደ።
5ያፌትም ጎሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ያዋን፥ ቱባል፥ ሜሼክና ቲራስ ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ 6የጎሜር ልጆች አሽከናዝ፥ ሪፋትና ቶጋርማ ናቸው። 7የያዋን ልጆች፥ ኤሊሻ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም እና ሮዳሂም ናቸው።
8የካም ወንዶች ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ እና ከነዓን ናቸው። 9የኩሽ ልጆች ሳባ፥ ሐዊላ፥ ሰብታ፥ ራዕማና ሳብተካ ናቸው፤ የራዕማ ወንዶች ልጆች ሳባና ድዳን ናቸው። 10ኩሽ ናምሩድን ወለደ፤ ናምሩድም በዓለም የመጀመሪያው ታዋቂ ጦረኛ ሆነ። 11የምጽራይም ልጆች ሉዲም፥ አናሚም፥ ሌሃቢም ናፍቱሔም፥ 12የፈትሩሲም፥ የከስሉሂምና የፍልስጥኤማውያን አባት የከፍቶሪም ሕዝቦች ናቸው። 13-16የከነዓን የበኲር ልጅ ጺዶን ሲሆን እንዲሁም ሒታውያን፥ ኢያቡሳውያን፥ አሞራውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ ሒዋውያን፥ ዓርቃውያን፥ ሲናውያን፥ አርዋዳውያን፥ ጸማራውያንና ሐማታውያን የከነዓን ልጆች ናቸው።
17የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ዑፅ፥ ሑል፥ ጌቴርና ሜሼክ ሲሆኑ፥ እነርሱም በስሞቻቸው ለሚጠሩ ሕዝቦች የነገድ አባቶች ናቸው። 18አርፋክስድ ሼላሕን ወለደ፤ ሼላሕም ዔቦርን ወለደ፤ 19ዔቦር ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ በእርሱ ዘመን የዓለም ሕዝቦች ስለ ተከፋፈሉ የመጀመሪያው ልጅ ፌሌቅ ተብሎ ተጠራ፤ ሁለተኛው ደግሞ ዮቅጣን ተብሎ ተጠራ። 20ዮቅጣን አልሞዳድን፥ ሼሌፍን፥ ሐጻርማዌትን፥ ዬራሕን፥ 21ሀዶራምን፥ ኡዛልን፥ ዲቅላን፥ 22ዔባልን፥ አቢማኤልን፥ ሳባን፥ 23ኦፊርን፥ ሐዊላና ዮባብን ወለደ። እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ።
24ከሴም እስከ አብራም ያለው የትውልድ ሐረግ ሴምን፥ አርፋክስድን፥ ሼላሕን፥ 25ዔቦርን፥ ፋሌቅን፥ ረዑን፥ 26ሰሩግን፥ ናኮርን፥ ታራንና 27በኋላ አብርሃም የተባለውን አብራምን ያጠቃልላል።
የእስማኤል ትውልድ
(ዘፍ. 25፥12-16)
28አብርሃም ይስሐቅንና እስማኤልን ወለደ፤ 29-30የእስማኤል ልጆች በእስማኤል በኵር ልጅ ስም የተጠራው ነባዮት፥ ቄዳር፥ አድበኤል፥ ሚብሣም፥ ሚሽማዕ፥ ዱማ፥ ማሣ፥ ሐዳድ፥ ቴማ፥ 31ይጡር፥ ናፊሽና ቄድማ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
32አብርሃም ቀጡራ ተብላ ከምትጠራው ቊባቱ ዚምራን፥ ዮቅሻን፥ መዳን፥ ምድያም፥ ዩሽባቅና ሹሐ ተብለው የሚጠሩትን ስድስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዮቅሻንም ሳባና ደዳን ተብለው የሚጠሩትን ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ 33ሚድያምም ዔፋ፥ ዔፌር፥ ሐኖክ፥ አቢዳዕና ኤልዳዓ ተብለው የሚጠሩትን አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ።
የዔሳው ትውልድ
(ዘፍ. 36፥1-19)
34የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ፥ ዔሳውንና ያዕቆብን ወለደ፤ 35ዔሳውም ኤሊፋዝን፥ ረዑኤልን፥ ይዑሽን፥ ያዕላምንና ቆሬን ወለደ፤ 36ኤሊፋዝም ቴማን፥ ኦማር፥ ጸፊ፥ ጋዕታም፥ ቀናዝ፥ ቲምናዕና፥ ዐማሌቅ ተብለው የሚጠሩትን ልጆች ወለደ። 37ረዑኤልም ናሐት፥ ዘራሕ፥ ሻማና፥ ሚዛ ተብለው የሚጠሩትን ልጆች ወለደ።
የመጀመሪያዎቹ የኤዶም ነዋሪዎች
(ዘፍ. 36፥20-30)
38-42የሤዒር ልጆች ሎጣን፥ ሸባል ጸባኦን፥ ዐና፥ ዲሾን፥ ኤጸርና ዲሻን ናቸው።
የሎጣን ልጆች ሖሪ፥ ሆማም ሲሆኑ፥ ቲምና የሎጣን እኅት ነበረች።
የሾባል ልጆች አልዋን፥ ማናሐት፥ ዔባል ሸፊ እና ኦናም ናቸው።
የጸባኦን ልጆች አያ እና አና ናቸው።
የአና ልጅ ዲሾን ነው።
የዲሾንም ልጆች ሔምዳን፥ ኤሽባን፥ ኢትራን እና ክራን ናቸው።
የኤጽር ልጆች ቢልሃን፥ ዛእዋን፥ ዓቃን ናቸው።
የዲሻን ልጆች ዑፅ እና አራን ናቸው።
የኤዶም ነገሥታት
(ዘፍ. 36፥31-43)
43በእስራኤል ምንም ንጉሥ ባልነገሠበት ዘመን የሚከተሉት ነገሥታት በኤዶም ምድር በየተራ ነግሠዋል፦ የከተማው ስም ዲንሃባ ይባል የነበረው የበዖር ልጅ ቤላዕ ነገሠ፤ 44ቤላዕም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ ባሶራዊው የዛራ ልጅ ዮባብ ነገሠ። 45ዩባብ በሞተ ጊዜ የቴማን አገር ሰው ሑሻም ነገሠ፥ 46ሑሻም በሞተ ጊዜ በሞአብ አገር ምድያምን ያሸነፈው የበዳድ ልጅ ሀዳድ ነገሠ፤ የከተማይቱም ስም አዊ ነበረ። 47ሀዳድ በሞተ ጊዜ የማሥሬቃ ተወላጅ የነበረው ሳምላ ነገሠ። 48ሳምላም በሞተ ጊዜ በኤፍራጥስ ወንዝ ዳር ያለችው የረሐቦት ተወላጅ የነበረው ነገሠ። 49ሻኡል በሞተ ጊዜ የዐክቦር ልጅ የነበረው በዓልሐናን ነገሠ። 50በዓልሐናን በሞተ ጊዜ የፋዑ ተወላጅ የነበረው ሀዳድ ነገሠ፤ ሚስቱም መሄጣብኤል የምትባል የዛሀብ የልጅ ልጅ የማናሬድ ልጅ ነበረች።
51ሃዳድም ሞተ የኤዶምም አለቆች ቲምናዕ፥ ዐልዋ፥ ዬቴት 52ኦሆሊባማ፥ ኤላ፥ ፊኖን፥ 53ቀናዝ፥ ቴማን፥ ሚብዳር፥ 54መግዲኤልና ዒራም ተብለው ይጠሩ ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ