አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል መግቢያ
መግቢያ
የዜና መዋዕል መጻሕፍት በሳሙኤልና በነገሥት መጻሕፍት የሰፈሩትን ታሪኮች በተለየ አቅጣጫ በድጋሚ የሚዘረዝር ነው፤ በዜና መዋዕል መጻሕፍት የእስራኤልን ንጉሣዊ መንግሥት ታሪክ በሚመለከት ሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች ተዘርዝረዋል።
1. የእስራኤልና የይሁዳ መንግሥታት በጥፋት ላይ የወደቁ ቢሆኑም እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጠውን የተስፋ ቃል ሁሉ ይጠብቅ እንደ ነበረና በይሁዳ በሚኖሩት አማካይነት ለሕዝቡ ያለውን ዕቅድ በሥራ ላይ ያውለው እንደ ነበር ለማሳየት ነው፤ ለዚህም ማረጋገጫ መሠረት እንዲሆን ጸሐፊው ዳዊትና ሰሎሞን ወዳከናወኑአቸው ታላላቅ ተግባሮች ኢዮሣፍጥ፥ ሕዝቅያስና ኢዮስያስ ወዳስገኙአቸው ተሐድሶዎችና ለእግዚአብሔር ያላቸውን ታማኝነት ወዳጸና ሕዝብ ያተኲራል።
2. በኢየሩሳሌም በነበረው ቤተ መቅደስ እግዚአብሔርን ማምለክ እንዴት እንደ ተጀመረ ለመግለጥ ነው፤ በተለይም የአምልኮው ሥርዓት ይካሄድበት የነበረው የካህናትና የሌዋውያን ድርጅት እንዴት እንደ ተቋቋመ ለማስረዳት ነበር፤ ቤተ መቅደሱን የሠራ ሰሎሞን ቢሆንም፥ የቤተ መቅደሱና የሥርዓተ አምልኮው መሥራች ዳዊት መሆኑን ለማስረዳት ነበር።
የመጽሐፉ አጠቃላይ ይዘት
የአዳም ዘሮች እስከ ንጉሥ ሳኦል ድረስ (ም. 1፥1—9፥44)
የሳኦልና የልጆቹ ሞት (ም. 10፥1-14)
የዳዊት መንገሥና ኢየሩሳሌምን መያዙ (11፥1-9)
ዝነኞቹ የዳዊት ወታደሮች (11፥10—12፥40)
የቃል ኪዳኑ ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም መወሰዱ (13፥1—16፥43)
ቤተ መቅደስን የሚሠራ ሰሎሞን ነው (17፥1-27)
የዳዊት ወታደራዊ ድሎች (18፥1—20፥8)
ዳዊት የሕዝብ ቈጠራ በማድረጉ የእግዚአብሔር ቊጣ (21፥1-30)
ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የተደረገ ዝግጅት (22፥1—28፥21)
ለቤተ መቅደሱ ሥራ የሕዝቡ ስጦታ (29፥1-20)
የሰሎሞን መንገሥ (29፥21-25)
የዳዊት ሞት (29፥26-30)
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997