እነርሱ ግን አምላክን ተፈታተኑት፤ በልዑልም ላይ ዐመፁ፤ ትእዛዙንም አልጠበቁም። ተመልሰው እንደ አባቶቻቸው ከዳተኛ ሆኑ፤ እንደማያስተማምን ጠማማ ቀስት ተወላገዱ። በኰረብታ ማምለኪያዎቻቸው አስቈጡት፤ ተቀርጸው በተሠሩ ጣዖቶቻቸው አስቀኑት። እግዚአብሔር ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ። በሰዎች መካከል ያቆማትን ድንኳን፣ የሴሎን ማደሪያ ተዋት። የኀይሉን ምልክት አስማረካት፤ ክብሩንም ለጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠ። ሕዝቡን ለሰይፍ ዳረገ፤ በርስቱም ላይ እጅግ ተቈጣ። ጕልማሶቻቸውን እሳት በላቸው፤ ልጃገረዶቻቸውም የሰርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም። ካህናታቸው በሰይፍ ተገደሉ፤ መበለቶቻቸውም ማልቀስ ተሳናቸው። ጌታም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤ የወይን ጠጅ ስካር እንደ በረደለት ጀግናም ብድግ አለ። ጠላቶቹን መትቶ ወደ ኋላ መለሳቸው፤ የዘላለም ውርደትም አከናነባቸው። የዮሴፍን ድንኳን ተዋት፤ የኤፍሬምንም ነገድ አልመረጠም። ነገር ግን የይሁዳን ነገድ፣ የወደዳትን የጽዮንን ተራራ መረጠ። መቅደሱን እንደ ታላቅ ከፍታ፣ ለዘላለም እንደ መሠረታት ምድር ሠራት። ባሪያውን ዳዊትን መረጠ፤ ከበጎች ጕረኖ ውስጥ ወሰደው፤ ለሕዝቡ ለያዕቆብ፣ ለርስቱም ለእስራኤል እረኛ ይሆን ዘንድ፣ የሚያጠቡ በጎችን ከመከተል አመጣው። እርሱም በቅን ልቡ ጠበቃቸው፤ ብልኀት በተሞላ እጁም መራቸው።
መዝሙር 78 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 78
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 78:56-72
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos