እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ከልብ እሻለሁ፤ ውሃ በሌለበት፣ በደረቅና በተራቈተ ምድር፣ ነፍሴ አንተን ተጠማች፤ ሥጋዬም አንተን ናፈቀች። ስለዚህ በመቅደስ ውስጥ አየሁህ፤ ኀይልህንና ክብርህንም ተመለከትሁ። ምሕረትህ ከሕይወት ይበልጣልና፤ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል። እንግዲህ፣ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፤ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ። ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤ አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል። በመኝታዬ ዐስብሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ።
መዝሙር 63 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 63
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 63:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos