የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 60:6-12

መዝሙር 60:6-12 NASV

እግዚአብሔር ከመቅደሱ ተናገረ፤ “ደስ እያለኝ ሴኬምን እከፋፍላለሁ፤ የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ። ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴ የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው። ሞዓብ የመታጠቢያ ገንዳዬ ነው፤ በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤ በፍልስጥኤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።” ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? ወደ ኤዶምያስ ማን ይመራኛል? አምላክ ሆይ፤ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰራዊታችንም ጋራ አትወጣም። በጠላት ላይ ድልን አቀዳጀን፤ የሰው ርዳታ ከንቱ ነውና። በእግዚአብሔር ክንደ ብርቱ እንሆናለን፤ ጠላቶቻችንን የሚረጋግጥልን እርሱ ነውና።