መዝሙር 60:6-12
መዝሙር 60:6-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ከመቅደሱ ተናገረ፤ “ደስ እያለኝ ሴኬምን እከፋፍላለሁ፤ የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ። ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴ የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው። ሞዓብ የመታጠቢያ ገንዳዬ ነው፤ በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤ በፍልስጥኤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።” ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? ወደ ኤዶምያስ ማን ይመራኛል? አምላክ ሆይ፤ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰራዊታችንም ጋራ አትወጣም። በጠላት ላይ ድልን አቀዳጀን፤ የሰው ርዳታ ከንቱ ነውና። በእግዚአብሔር ክንደ ብርቱ እንሆናለን፤ ጠላቶቻችንን የሚረጋግጥልን እርሱ ነውና።

መዝሙር 60:6-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር በመቅደሱ ሆኖ እንዲህ አለ፦ “ድል አድርጌ ሴኬምን እሸነሽናለሁ፤ የሱኮትንም ሸለቆ ለሕዝቤ አከፋፍላለሁ። ገለዓድና ምናሴ የእኔ ናቸው፤ ኤፍሬም የራሴ መከላከያ ቊር ነው፤ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው። ሞአብ መታጠቢያዬ ነው፤ ኤዶም የእኔ መሆኑን ለማረጋገጥ ጫማዬን አኖርበታለሁ፤ በፍልስጥኤማውያንም ላይ።” ወደተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? እስከ ኤዶምስ ማን ይመራኛል? አምላክ ሆይ! አንተ ጥለኸናል፤ ከሠራዊታችንም ጋር ወደ ጦር ሜዳ መውጣት ትተሃል። የሰው ርዳታ ከንቱ ነው። ስለዚህ ጠላቶቻችንን ድል እንድናደርግ አንተ እርዳን። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ እናሸንፋለን፤ እርሱ ጠላቶቻችንን ያዋርዳቸዋል።
መዝሙር 60:6-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው። ወዳጆችህ እንዲድኑ በቀኝህ አድን፥ አድምጠኝም። እግዚአብሔር በቅድስናው ተናገረ፥ “በድል መንፈስ፥ ሴኬምንም እከፋፍላለሁ፥ የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ። ገለዓድ የእኔ ነው፥ ምናሴም የእኔ ነው፥ ኤፍሬም የራሴ ቁር ነው። ይሁዳ ንጉሤ በትሬ ነው፥ ሞዓብ መታጠቢያ ሳህኔ ነው፥ በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እዘረጋለሁ፥ በፍልስጥኤም ላይ በድል እጮኻለሁ። ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወስደኛል? ማንስ እስከ ኤዶምያስ ይመራኛል?” አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።