የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 35:19-28

መዝሙር 35:19-28 NASV

ከምድር ተነሥተው ጠላቶቼ የሆኑት፣ በላዬ ደስ አይበላቸው፤ እንዲያው የሚጠሉኝ፣ በዐይናቸው አይጣቀሱብኝ። የሰላም ንግግር ከአፋቸው አይወጣም፤ ዳሩ ግን በምድሪቱ በጸጥታ በሚኖሩት ላይ፣ ነገር ይሸርባሉ። አፋቸውን አስፍተው ከፈቱብኝ፤ “ዕሠይ! ዕሠይ! በዐይናችን አየነው” አሉ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን አይተሃልና ዝም አትበል፤ ጌታ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ። አምላኬ፣ ጌታዬ፤ ለእኔ ለመሟገት ተነሥ! ልትከራከርልኝም ተንቀሳቀስ። እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ በጽድቅህ ፍረድልኝ፤ በእኔም ላይ ደስ አይበላቸው። በልባቸው፣ “ዕሠይ! ያሰብነው ተሳካ! ዋጥ አደረግነውም” አይበሉ። በጭንቀቴ ደስ የሚላቸው፣ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤ በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ ዕፍረትንና ውርደትን ይከናነቡ። ፍትሕ ማግኘቴን የሚወድዱ፣ እልል ይበሉ፤ ሐሤትም ያድርጉ፤ ዘወትርም፣ “የባሪያው ሰላም ደስ የሚለው፣ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል!” ይበሉ። አንደበቴ ጽድቅህን፣ ምስጋናህንም ቀኑን ሙሉ ይናገራል።