መዝሙር 29
29
መዝሙር 29
ለማዕበሉ ጌታ የቀረበ ውዳሴ
የዳዊት መዝሙር።
1እናንተ ኀያላን፣ ለእግዚአብሔር ስጡ፤
ክብርንና ብርታትን ለእግዚአብሔር ስጡ።
2ለስሙ የሚገባ ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤
በቅድስናው ግርማ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
3 የእግዚአብሔር ድምፅ በውሆች ላይ ነው፤
የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤
እግዚአብሔር በታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ።
4 የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤
የእግዚአብሔር ድምፅ ግርማዊ ነው።
5 የእግዚአብሔር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤
እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይሰባብራል።
6ሊባኖስን እንደ ጥጃ፣
ስርዮንንም#29፥6 አርሞንዔም የተባለው ተራራ ነው። እንደ አውራሪስ ግልገል ያዘልላል።
7 የእግዚአብሔር ድምፅ
የእሳት ነበልባል ይረጫል።
8 የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤
የእግዚአብሔር ድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
9 የእግዚአብሔር ድምፅ ወርካዎችን ይወዘውዛል፤#29፥9 ወይም እግዚአብሔር አጋዘን እንድትወልድ ያደርጋል
ጫካዎችንም ይመነጥራል፤
ሁሉም በእርሱ ቤተ መቅደስ ሆኖ “ይክበር!” ይላል።
10 እግዚአብሔር በጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጧል፤#29፥10 ወይም ይቀመጣል
እግዚአብሔር በንጉሥነቱ ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።
11 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታትን ይሰጣል፤
እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።
Currently Selected:
መዝሙር 29: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.