እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ነቀፋ እንደ መሆኔ፣ አንተው ፍረድልኝ። ወዲያ ወዲህ ሳልልም፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈትነኝ፤ መርምረኝም፤ ልቤንና ውስጤን መርምር፤ ምሕረትህ ከፊቴ አልተለየምና፣ በእውነትህም ተመላለስሁ። ከማይረቡ ጋራ አልተቀመጥሁም፤ ከግብዞችም ጋራ አልተባበርሁም። የክፉዎችን ማኅበር ተጸየፍሁ፤ ከዐመፀኞችም ጋራ አልቀመጥም። እጆቼን በየዋህነት እታጠባለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መሠዊያህንም እዞራለሁ፤ የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፣ ታምራትህንም አወራ ዘንድ ነው።
መዝሙር 26 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 26
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 26:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos