መዝሙር 26:1-7
መዝሙር 26:1-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ነቀፋ እንደ መሆኔ፣ አንተው ፍረድልኝ። ወዲያ ወዲህ ሳልልም፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈትነኝ፤ መርምረኝም፤ ልቤንና ውስጤን መርምር፤ ምሕረትህ ከፊቴ አልተለየምና፣ በእውነትህም ተመላለስሁ። ከማይረቡ ጋራ አልተቀመጥሁም፤ ከግብዞችም ጋራ አልተባበርሁም። የክፉዎችን ማኅበር ተጸየፍሁ፤ ከዐመፀኞችም ጋራ አልቀመጥም። እጆቼን በየዋህነት እታጠባለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መሠዊያህንም እዞራለሁ፤ የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፣ ታምራትህንም አወራ ዘንድ ነው።
መዝሙር 26:1-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔር ያበራልኛል፥ ያድነኛልም፤ ምን ያስፈራኛል? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ ምን ያስደነግጠኛል? ክፉዎች ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ የሚያሠቃዩኝ እነዚያ ጠላቶቼ ደከሙ፥ ወደቁም። ሠራዊትም ቢጠላኝ ልቤ አይፈራብኝም፤ ሠራዊትም ቢከቡኝ በእርሱ እተማመናለሁ። እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት፥ እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ በቤተ መቅደሱም አገለግል ዘንድ። በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሸሽጎኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሰውሮኛልና፥ በዓለትም ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና። እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤ ዞርሁ በድንኳኑም መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ እልልም አልሁለት እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ እዘምርለትማለሁ። አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ፤ ማረኝ፥ አድምጠኝም።
መዝሙር 26:1-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ሆይ! በቅንነትና ባለማወላወል በአንተ ተማምኜ ስለ ኖርኩ ፍረድልኝ። እግዚአብሔር ሆይ! ፈትነኝ፤ ምኞቴንና ሐሳቤንም መርምር። የማያቋርጠው ፍቅርህ በዐይኖቼ ፊት ነው፤ ዘወትር የሚመራኝም የአንተ ታማኝነት ነው። ከአታላዮች ጋር አልወዳጅም፤ ከግብዞችም ጋር አልተባበርም፤ የክፉ አድራጊዎችን ጉባኤ እጠላለሁ፤ ከክፉዎችም ጋር መቀመጥ አልፈቅድም። እግዚአብሔር ሆይ! ንጹሕነቴን ለማሳየት እጆቼን እታጠባለሁ፤ መሠዊያህንም በመዞር አንተን አመልካለሁ። የምስጋና መዝሙር እየዘመርኩ፥ የአንተን ድንቅ ሥራዎች ሁሉ እናገራለሁ።
መዝሙር 26:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
አቤቱ፥ እኔ በቅንነት ሄጃለሁና ፍረድልኝ፥ በጌታም አምኛለሁና አልናወጥም። አቤቱ፥ ፈትነኝ መርምረኝም፥ ኩላሊቴንና ልቤን መርምር። ቸርነትህ በዓይኔ ፊት ነውና፥ በእውነትህም ተመላለስሁ። ከአታላዮች ጋር አልተቀመጥሁም፥ ከአስመሳዮችም ጋር አልገባሁም። የክፉ አድራጊዎቸን ማኅበር ጠላሁ፥ ከክፉዎችም ጋር አልቀመጥም። እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፥ አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥ የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ።