ስምህን ለወንድሞቼ ዐውጃለሁ፤ በጉባኤም መካከል አወድስሃለሁ። እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ፤ አወድሱት፤ እናንተ የያዕቆብ ዘር ሁላችሁ፤ አክብሩት፤ የእስራኤልም ዘር ሁላችሁ፤ እርሱን ፍሩት። እርሱ የተጨነቀውን ሰው ጭንቀት፣ አልናቀም፤ ቸልም አላለምና፤ ፊቱንም ከርሱ አልሰወረም፤ ነገር ግን ድረስልኝ ብሎ ሲጮኽ ሰማው። በታላቅ ጉባኤ የማቀርበው ምስጋናዬ ከአንተ የመጣ ነው፤ እርሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ። ምስኪኖች በልተው ይጠግባሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹትም ያመሰግኑታል፤ ልባችሁም ለዘላለም ሕያው ይሁን! የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስታውሳሉ፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ፤ የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ፣ በፊቱ ይሰግዳሉ። መንግሥት የእግዚአብሔር ናትና፤ ሕዝቦችንም የሚገዛ እርሱ ነው። የምድር ከበርቴዎች ይበላሉ፤ ይሰግዱለታልም፤ ነፍሱን በሕይወት ማቈየት የማይችለው፣ ወደ ዐፈር ተመላሽ የሆነው ሁሉ በፊቱ ይንበረከካል። የኋለኛው ትውልድ ያገለግለዋል፤ ለመጪው ትውልድ ስለ ጌታ ይነገረዋል። ገና ላልተወለደ ሕዝብ፣ ጽድቁን ይነግራሉ፤ እርሱ ይህን አድርጓልና።
መዝሙር 22 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 22
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 22:22-31
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos