የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 22:22-31

መዝሙር 22:22-31 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ስምህን ለወንድሞቼ ዐውጃለሁ፤ በጉባኤም መካከል አወድስሃለሁ። እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ፤ አወድሱት፤ እናንተ የያዕቆብ ዘር ሁላችሁ፤ አክብሩት፤ የእስራኤልም ዘር ሁላችሁ፤ እርሱን ፍሩት። እርሱ የተጨነቀውን ሰው ጭንቀት፣ አልናቀም፤ ቸልም አላለምና፤ ፊቱንም ከርሱ አልሰወረም፤ ነገር ግን ድረስልኝ ብሎ ሲጮኽ ሰማው። በታላቅ ጉባኤ የማቀርበው ምስጋናዬ ከአንተ የመጣ ነው፤ እርሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ። ምስኪኖች በልተው ይጠግባሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹትም ያመሰግኑታል፤ ልባችሁም ለዘላለም ሕያው ይሁን! የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስታውሳሉ፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ፤ የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ፣ በፊቱ ይሰግዳሉ። መንግሥት የእግዚአብሔር ናትና፤ ሕዝቦችንም የሚገዛ እርሱ ነው። የምድር ከበርቴዎች ይበላሉ፤ ይሰግዱለታልም፤ ነፍሱን በሕይወት ማቈየት የማይችለው፣ ወደ ዐፈር ተመላሽ የሆነው ሁሉ በፊቱ ይንበረከካል። የኋለኛው ትውልድ ያገለግለዋል፤ ለመጪው ትውልድ ስለ ጌታ ይነገረዋል። ገና ላልተወለደ ሕዝብ፣ ጽድቁን ይነግራሉ፤ እርሱ ይህን አድርጓልና።

መዝሙር 22:22-31 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የስምህን ታላቅነት ለወገኖቼ እናገራለሁ፤ እነርሱ በተሰበሰቡበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩት አመስግኑት! እናንተ የያዕቆብ ዘሮች ሁሉ አክብሩት! እናንተ የእስራኤል ዘሮች ሁሉ በፍርሃት ከፍ ከፍ አድርጉት! የተጨቈነውን ሰው አልናቀውም፤ በሁናቴውም አልተጸየፈውም፤ ፊቱን ከእርሱ አልሰወረም፤ ነገር ግን ለእርዳታ የሚያደርገውን ጩኸት አዳመጠው። ስለ ሠራኸው መልካም ሥራ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ፤ በሚፈሩህ ሰዎች ፊት ሆኜ፥ የተሳልኩትን ስለት እፈጽማለሁ። ድኾች እስኪጠግቡ ይበላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹት ያመሰግኑታል፤ ልባቸው በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ይደሰታል። እስከ ምድር ዳርቻ ያሉ ሰዎች ሁሉ አስታውሰው ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ በዓለም የሚገኙት ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ። ሥልጣን ሁሉ የአንተ ነው፤ ሕዝቦችም ሁሉ ይገዙልሃል። ጌታ ሆይ! የተትረፈረፈ ሀብት ያላቸው ሁሉ ይሰግዱልሃል። ለሞትና ለመቃብር የተቃረቡትም መጥተው ይንበረከኩልሃል። መጪው ትውልድ ያገለግለዋል፤ የወደፊት ትውልድም ስለ እግዚአብሔር ይነገረዋል። እነርሱ የጽድቅ ሥራውን በማወጅ “እግዚአብሔር ሕዝቡን አዳነ” ብለው ገና ላልተወለዱ ሰዎች ይናገራሉ።

መዝሙር 22:22-31 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ከአንበሳ አፍ አድነኝ፥ ከጐሽ ቀንድም ጠብቀኝ፥ መለስክልኝ! ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ፥ በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ። ጌታን የምትፈሩ፥ አመስግኑት፥ የያዕቆብ ዘር ሁላችሁ፥ አክብሩት፥ የእስራኤልም ዘር ሁላችሁ፥ ፍሩት። የችግረኛን ችግር አልናቀምና፥ ቸልም አላለምና፥ ፊቱንም አልሰወረምና፥ ነገር ግን ወደ እርሱ በጮኸ ጊዜ ሰማው። በታላቅ ጉባኤ ምስጋናዬ ከአንተ ዘንድ ነው። እርሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እሰጣለሁ። ችግረኞች ይበላሉ፥ ይጠግቡማል፥ ጌታንም የሚሹት ያመሰግኑታል፥ ልባቸውም ለዘለዓለም ሕያው ይሁን። የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስቡ፥ ወደ ጌታም ይመለሱ፥ የአሕዛብ ነገዶች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ። መንግሥት ለጌታ ነውና፥ እርሱም አሕዛብን ይገዛል። የምድር ደንዳኖች ሁሉ ይበላሉ ይሰግዳሉም፥ ወደ መሬት የሚወርዱት ሁሉ በፊቱ ይንበረከካሉ፥ ነፍሴም ስለ እርሱ በሕይወት ትኖራለች። ትውልድ ይገዛለታል፥ የሚመጣው ትውልድ ስለ ጌታ ይነገረዋል፥