የአባቶቹ በደል በእግዚአብሔር ፊት ይታሰብ፤ የእናቱም ኀጢአት አይደምሰስ። መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፉ ዘንድ፣ ኀጢአታቸው ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ይኑር። ድኻውንና ችግረኛውን፣ ልቡም የቈሰለውን፣ እስከ ሞት አሳደደ እንጂ፣ ምሕረት ያደርግ ዘንድ አላሰበምና። መራገምን ወደደ፤ ወደ እርሱም መጣች፤ በመባረክ ደስ አልተሠኘም፤ በረከትም ከርሱ ራቀች። መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፤ እርሷም እንደ ውሃ ወደ ውስጥ ሰውነቱ፣ እንደ ዘይትም ወደ ዐጥንቱ ዘለቀች። ገላውን እንደሚሸፍንበት ልብስ፣ ዘወትር እንደሚታጠቀውም መቀነት ትሁነው። እግዚአብሔር ለሚወነጅሉኝ ሰዎች፣ በነፍሴም ላይ ክፉ ለሚናገሩ የሚከፍላቸው ይኸው ይሁን። አንተ ግን ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ስምህ በበጎ ተመልከተኝ፤ ምሕረትህም መልካም ናትና አድነኝ። እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና፤ ልቤም በውስጤ ቈስሏልና። እንደ ምሽት ጥላ ከእይታ ተሰውሬአለሁ፤ እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ። ከጾም የተነሣ ጕልበቴ ዛለ፤ ሰውነቴም ከስቶ ዐመድ ለበሰ። ለመሣለቂያ ሆንሁላቸው፤ ሲያዩኝም ራሳቸውን ይነቀንቃሉ። እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ርዳኝ፤ እንደ ምሕረትህም አድነኝ። እግዚአብሔር ሆይ፤ እጅህ ይህን እንዳደረገች፣ አንተም ይህን እንደ ፈጸምህ ይወቁ። እነርሱ ይራገማሉ፤ አንተ ግን ትባርካለህ፤ በሚነሡበት ጊዜ ይዋረዳሉ፤ ባሪያህ ግን ሐሤት ያደርጋል። የሚወነጅሉኝ ውርደትን ይከናነቡ፤ ዕፍረትንም እንደ ሸማ ይልበሱ። እግዚአብሔርን በአንደበቴ እጅግ አመሰግናለሁ፤ በታላቅ ሕዝብም መካከል አወድሰዋለሁ። በነፍሱ ላይ ከሚፈርዱት ያድነው ዘንድ፣ እርሱ በችግረኛው ቀኝ በኩል ይቆማልና።
መዝሙር 109 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 109
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 109:14-31
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos