የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 109:14-31

መዝሙር 109:14-31 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የአባቶቹ በደል በእግዚአብሔር ፊት ይታሰብ፤ የእናቱም ኀጢአት አይደምሰስ። መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፉ ዘንድ፣ ኀጢአታቸው ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ይኑር። ድኻውንና ችግረኛውን፣ ልቡም የቈሰለውን፣ እስከ ሞት አሳደደ እንጂ፣ ምሕረት ያደርግ ዘንድ አላሰበምና። መራገምን ወደደ፤ ወደ እርሱም መጣች፤ በመባረክ ደስ አልተሠኘም፤ በረከትም ከርሱ ራቀች። መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፤ እርሷም እንደ ውሃ ወደ ውስጥ ሰውነቱ፣ እንደ ዘይትም ወደ ዐጥንቱ ዘለቀች። ገላውን እንደሚሸፍንበት ልብስ፣ ዘወትር እንደሚታጠቀውም መቀነት ትሁነው። እግዚአብሔር ለሚወነጅሉኝ ሰዎች፣ በነፍሴም ላይ ክፉ ለሚናገሩ የሚከፍላቸው ይኸው ይሁን። አንተ ግን ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ስምህ በበጎ ተመልከተኝ፤ ምሕረትህም መልካም ናትና አድነኝ። እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና፤ ልቤም በውስጤ ቈስሏልና። እንደ ምሽት ጥላ ከእይታ ተሰውሬአለሁ፤ እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ። ከጾም የተነሣ ጕልበቴ ዛለ፤ ሰውነቴም ከስቶ ዐመድ ለበሰ። ለመሣለቂያ ሆንሁላቸው፤ ሲያዩኝም ራሳቸውን ይነቀንቃሉ። እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ርዳኝ፤ እንደ ምሕረትህም አድነኝ። እግዚአብሔር ሆይ፤ እጅህ ይህን እንዳደረገች፣ አንተም ይህን እንደ ፈጸምህ ይወቁ። እነርሱ ይራገማሉ፤ አንተ ግን ትባርካለህ፤ በሚነሡበት ጊዜ ይዋረዳሉ፤ ባሪያህ ግን ሐሤት ያደርጋል። የሚወነጅሉኝ ውርደትን ይከናነቡ፤ ዕፍረትንም እንደ ሸማ ይልበሱ። እግዚአብሔርን በአንደበቴ እጅግ አመሰግናለሁ፤ በታላቅ ሕዝብም መካከል አወድሰዋለሁ። በነፍሱ ላይ ከሚፈርዱት ያድነው ዘንድ፣ እርሱ በችግረኛው ቀኝ በኩል ይቆማልና።

መዝሙር 109:14-31 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር የቀድሞ አባቶቹን ኃጢአት ያስብበት፤ የእናቱንም ኃጢአት ይቅር አይበልላት። እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ዘወትር ያስታውስ፤ እነርሱ ራሳቸው ግን ፈጽሞ የተረሱ ይሁኑ። ሰውየው ደግ ሥራ ለማድረግ ፈጽሞ አላሰበም፤ ድኾችን፥ ችግረኞችንና ምስኪኖችን እያሳደደ ይገድል ነበር። መራገም ይወድ ስለ ነበር፥ እርሱም የተረገመ ይሁን፤ መመረቅን ይጠላ ስለ ነበር፥ እርሱንም የሚመርቅ ሰው አይኑር። መራገም ልብስ የመልበስ ያኽል ይቀልለው ነበር፤ ስለዚህ የራሱ ርግማን እንደ ውሃ ወደ ሰውነቱ ገብቶ ያረስርሰው፤ እንደ ዘይትም ወደ አጥንቱ ዘልቆ ይግባ። እንደ ልብስ ይሸፍነው፤ እንደ ቀበቶም ዘወትር በወገቡ ዙሪያ ይሁን። እግዚአብሔር ሆይ! ይህን ሁሉ ክፉ ነገር በእኔ ላይ የሚናገሩትን ጠላቶቼን በዚህ ዐይነት ቅጣቸው። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ለክብርህ ተገቢ የሆነውን አድርግልኝ፤ ዘለዓለማዊው ፍቅርህም ድንቅ ስለ ሆነ አድነኝ። እኔ ድኻና ምስኪን ነኝ፤ የደረሰብኝም መከራ ልቤን አቊስሎታል። እንደ ማታ ጥላ ላልፍ ተቃርቤአለሁ፤ እንደ አንበጣም በነፋስ ተወስጄአለሁ። ጒልበቶቼ በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ። ጠላቶቼ እኔን በማየት ይስቃሉ፤ በንቀትም ራሳቸውን ይነቀንቃሉ። እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እባክህ እርዳኝ፤ ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህም አድነኝ። የምታድነኝ አንተ ብቻ እንደ ሆንክ ጠላቶቼ እንዲያውቁ አድርግ። እነርሱ ይረግሙኛል፤ አንተ ግን ትመርቀኛለህ፤ አሳዳጆቼን አዋርዳቸው፤ እኔን አገልጋይህን ግን ደስ አሰኘኝ። ጠላቶቼ ውርደትን እንደ ልብስ ይልበሱ፤ ኀፍረትንም እንደ መጐናጸፊያ ይደርቡ። ድምፄን ከፍ አድርጌ ለእግዚአብሔር ክብር እሰጣለሁ፤ በሕዝብ ጉባኤ መካከል አመሰግነዋለሁ። ምክንያቱም እርሱ ሊገድሉት ከተዘጋጁ ሰዎች እጅ ሊያድነው ስለ ድኻ ሰው መብት ይከራከራል፤

መዝሙር 109:14-31 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የአባቶቹ ጥፋት በጌታ ፊት ትታወስ፥ የእናቱም ኃጢአት አትደምሰስ። በጌታ ፊት ሁልጊዜ ይኑሩ፥ መታሰቢያቸውም ከምድረ ገጽ ይጥፋ። በቸርነት ለመመላለስ አላሰበምና፥ ችግረኛንና ምስኪንን ልቡ የተሰበረውንም ለመግደል ያሳድድ ነበር። መራገምን ወደደ፥ ወደ እርሱም መጣች፥ በረከትንም አልመረጠም፥ ከእርሱም ራቀች። መራገምን እንደ ልብስ ለበሳት፥ እንደ ውኃም ወደ አንጀቱ፥ እንደ ቅባትም ወደ አጥንቱ ገባች። እንደሚለብሰው ልብስ፥ ሁልጊዜም እንደሚታጠቀው ትጥቅ ትሁነው። ይህ ቅጣት በሚከሱኝና በነፍሴም ላይ ክፉን በሚናገሩ ላይ ከጌታ ዘንድ ይሁን። አንተ ግን አቤቱ ጌታዬ፥ ስለ ስምህ ስትል ታደገኝ፥ ጽኑ ፍቅርህ መልካም ናትና አድነኝ። እኔ ችግረኛ ምስኪንም ነኝና፥ በውስጤም ልቤ ቆስሎአል። እንዳለፈ ጥላ አለቅሁ፥ እንደ አንበጣም እረገፍሁ። ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ፥ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ። እኔም በእነርሱ ዘንድ መሳለቂያ ሆንሁ፥ ሲያዩኝ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ። አቤቱ አምላኬ፥ እርዳኝ፥ እንደ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ። አቤቱ፥ እጅህ ይህች መሆኗን፥ አንተም ይህንን እንዳደረግህ ይወቁ። እነርሱ ይራገማሉ አንተ ግን ትባርካለህ፥ በእኔ ላይ የሚነሡ ይፈሩ፥ አገልጋይህ ግን ደስ ይበለው። የሚከሱኝ እፍረትን ይልበሱ፥ እፍረታቸውን እንደ መጐናጸፊያ ይልበሱአት። ጌታን በአፌ እጅግ አመሰግነዋለሁ። በብዙዎችም መካከል አከብረዋለሁ፥ ነፍሱን ከሚያሳድዱአት ያድን ዘንድ ከድሀ በኩል ቆሞአልና።