ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ ሄደ፤ ሌዊ የተባለ አንድ ቀረጥ ሰብሳቢም በቀረጥ መሰብሰቢያው ቦታ ተቀምጦ አየውና፣ “ተከተለኝ” አለው፤ እርሱም ሁሉን ትቶ ተነሥቶ ተከተለው። ሌዊም ለኢየሱስ በቤቱ ትልቅ ግብዣ አደረገ፤ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ሌሎች ሰዎችም ከእነርሱ ጋራ በማእድ ተቀምጠው ነበር። ፈሪሳውያንና ጸሐፍታቸውም “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ‘ከኀጢአተኞች’ ጋራ የምትበሉትና የምትጠጡት ለምንድን ነው?” እያሉ በደቀ መዛሙርቱ ላይ አጕረመረሙ። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፤ እኔም ኀጢአተኞችን ወደ ንስሓ ልመልስ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም።”
ሉቃስ 5 ያንብቡ
ያዳምጡ ሉቃስ 5
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሉቃስ 5:27-32
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos