ከኢየሱስ ጋራ በማእድ ከተቀመጡት መካከል አንዱ ይህን ሰምቶ “በእግዚአብሔር መንግሥት ቀርቦ ከማእድ የሚበላ ምስጉን ነው” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “አንድ ሰው ትልቅ ግብዣ አዘጋጅቶ ብዙ ሰው ጠራ፤ የግብዣውም ሰዓት በደረሰ ጊዜ የተጋበዙትን እንግዶች፣ ‘እነሆ፤ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቷልና ኑ’ ብሎ እንዲጠራ ባሪያውን ላከባቸው። “ነገር ግን ሁሉም የየራሳቸውን ምክንያት ይፈጥሩ ጀመር፤ አንደኛው፣ ‘ገና አሁን መሬት ስለ ገዛሁ ሄጄ ማየት አለብኝ፤ እባክህ፣ ይቅርታ አድርግልኝ’ አለው። “ሌላውም፣ ‘ዐምስት ጥማድ በሬዎች ገዝቻለሁ፤ እነርሱን ልፈትናቸው ስለ ሆነ እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ’ አለ። “ሌላው ደግሞ፣ ‘ገና ሙሽራ ስለ ሆንሁ ልመጣ አልችልም’ አለ። “ባሪያውም ተመልሶ መጥቶ ይህንኑ ለጌታው ነገረው። በዚህ ጊዜ የቤቱ ጌታ ተቈጥቶ አገልጋዩን፣ ‘ቶሎ ብለህ ወደ ከተማው አውራ ጐዳናዎችና መተላለፊያ መንገዶች ውጣ፤ ድኾችንና አካለ ስንኩሎችን፣ ዐይነ ስውሮችንና ዐንካሶችን ወደዚህ አስገባቸው’ አለው። “ባሪያውም፣ ‘ጌታዬ፤ ያዘዝኸው ሁሉ ተፈጽሟል፤ ገና አሁንም ቦታ አለ’ አለው። “ጌታውም ባሪያውን፣ ‘ወደ ጐዳናዎች እና በዐጥሮች መካከል ወዳሉ መንገዶች ውጣ፤ ቤቴም እንዲሞላ ያገኘኸውን ሁሉ በግድ አምጥተህ አስገባ፤ እላችኋለሁና ከተጋበዙት ከእነዚያ ሰዎች መካከል አንድ ሰው እንኳ ግብዣዬን አይቀምስም አለው።’ ”
ሉቃስ 14 ያንብቡ
ያዳምጡ ሉቃስ 14
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሉቃስ 14:15-24
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos