ዘሌዋውያን 9:22-24

ዘሌዋውያን 9:22-24 NASV

አሮንም እጆቹን ወደ ሕዝቡ ዘርግቶ ባረካቸው፤ የኀጢአት መሥዋዕቱን፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረቱን መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ ወረደ። ከዚህ በኋላ፣ ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ገቡ፤ ከዚያ ሲወጡም ሕዝቡን ባረኩ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ። እሳት ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥቶ፣ በመሠዊያው ላይ የነበረውን በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ ይህን ባዩ ጊዜ እልል አሉ፤ በግንባራቸውም ተደፉ።