የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢዮብ 19:23-29

ኢዮብ 19:23-29 NASV

“ምነው ቃሌ በተጻፈ ኖሮ! በመጽሐፍም በታተመ! ምነው በብረትና በእርሳስ በተጻፈ ኖሮ! በዐለትም ላይ በተቀረጸ! የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፣ በመጨረሻም በምድር ላይ እንደሚቆም ዐውቃለሁ። ቈዳዬ ቢጠፋም፣ ከሥጋዬ ብለይም፣ እግዚአብሔርን አየዋለሁ፤ ሌላ ሳይሆን እኔው በገዛ ዐይኔ፣ እኔ ራሴ አየዋለሁ፤ ልቤ በውስጤ ምንኛ በጉጉት ዛለ! “ ‘የችግሩ መንሥኤ በውስጡ አለ፤ እኛ እንዴት እናሳድደዋለን?’ ብትሉ፣ ቍጣ በሰይፍ መቀጣትን ያስከትላልና፣ ራሳችሁ ሰይፍን ፍሩ፤ በዚያ ጊዜ ፍርድ እንዳለ ታውቃላችሁ።”