የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 64

64
1አቤቱ፤ ሰማያትን ቀድደህ ምነው በወረድህ!
ምነዋ ተራሮች በፊትህ በተናወጡ!
2እሳት ሲለኰስ ጭራሮን እንደሚያቀጣጥል፣
ውሃንም እንደሚያፈላ፣
ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ ውረድ፤
መንግሥታትም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ አድርግ።
3እኛ ያልጠበቅነውን አስፈሪ ነገር ባደረግህ ጊዜ፣
አንተ ወረድህ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።
4ከጥንት ጀምሮ፣
በተስፋ ለሚጠባበቁት የሚደርስላቸው፣
እንደ አንተ ያለውን አምላክ ያየ ዐይን፣
ያደመጠ ጆሮ ፈጽሞ አልነበረም።
5በደስታ ቅን ነገር የሚያደርጉትን፣
መንገድህን የሚያስቡትንም ትረዳለህ፤
እኛ ግን በእነርሱ ላይ ሳናቋርጥ ኀጢአት በመሥራታችን፣
እነሆ፤ ተቈጣህ፤
ታዲያ እንዴት መዳን እንችላለን?
6ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤
የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤
ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤
ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።
7ማንም በጸሎት ስምህን አይጠራም፤
አንተንም ለመያዝ የሚሞክር የለም፤
ፊትህን ከእኛ ሰውረሃል፤
ስለ ኀጢአታችንም ትተኸናል።
8ይህም ሆኖ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አባታችን ነህ፤
እኛ ሸክላዎች፣ አንተም ሸክላ ሠሪ ነህ፤
ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን፤
9 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከልክ በላይ አትቈጣን፤
ኀጢአታችንንም ለዘላለም አታስብ፤
እባክህ ተለመነን፤ ፊትህን ወደ እኛ መልስ፤
ሁላችንም የአንተ ሕዝብ ነንና።
10የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆኑ፤
ጽዮን ራሷ እንኳ ምድረ በዳ፣ ኢየሩሳሌምም የተፈታች ሆናለች።
11አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰውና የተከበረው ቤተ መቅደሳችን፣
በእሳት ተቃጥሏል፤
ያማሩ ቦታዎቻችንም ሁሉ እንዳልነበር ሆነዋል።
12 እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ አትመለስምን?
ዝም ብለህ ከልክ በላይ ትቀጣናለህን?

Currently Selected:

ኢሳይያስ 64: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ