ዘፀአት 35:10-21

ዘፀአት 35:10-21 NASV

“በመካከላችሁ ጥበበኞች የሆኑ ሁሉ መጥተው እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ይሥሩ፦ “የመገናኛውን ድንኳን ከነድንኳኑና ከነመደረቢያው፣ ማያያዣዎችን፣ ክፈፎችን፣ አግዳሚዎችን፣ ቋሚዎችንና መሠረቶችን፤ ታቦቱን ከነመሎጊያዎቹ፣ የስርየት መክደኛውንና የሚሸፍነውን መጋረጃ፤ ጠረጴዛውን ከነመሎጊያዎቹ፣ ዕቃዎቹን ሁሉና የገጸ ኅብስቱን፤ ለመብራት የሆነውን መቅረዝ ከነዕቃዎቹ፣ ቀንዲሎችንና ለመብራት የሚሆነውን ዘይት፤ የዕጣን መሠዊያውን ከነመሎጊያዎቹ፣ ቅብዐ ዘይቱንና ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን፤ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ የሚሆነውን የመግቢያ መጋረጃ፤ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን ከንሓስ መጫሪያው፣ መሎጊያዎቹንና ዕቃዎቹን ሁሉ፣ የንሓስ ሰኑን ከነማስቀመጫው፣ የአደባባዩን መጋረጃዎች ከነምሰሶዎቻቸውና ከነመሠረቶቹ፣ የአደባባዩን መግቢያ መጋረጃ፤ ለመገናኛው ድንኳንና ለአደባባዩ የሚሆኑ የድንኳን ካስማዎችና ገመዶቻቸው፤ በመቅደሱ ውስጥ ለማገልገል የሚለበሱ የፈትል ልብሶችን ይኸውም የካህኑ የአሮንን የተቀደሱ ልብሶችንና ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚለብሷቸውን የወንዶች ልጆቹን ልብሶች ይሥሩ።” ከዚያም የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጡ፤ ፈቃደኛ የነበረና ልቡን ያነሣሣው ሁሉ በመምጣት ለመገናኛው ድንኳን ሥራ፣ ለአገልግሎቱ ሁሉና ለተቀደሱ ልብሶች የሚሆን ለእግዚአብሔር መባ አመጡ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}