ዘፀአት 35:10-21
ዘፀአት 35:10-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“በመካከላችሁ ጥበበኞች የሆኑ ሁሉ መጥተው እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ይሥሩ፦ “የመገናኛውን ድንኳን ከነድንኳኑና ከነመደረቢያው፣ ማያያዣዎችን፣ ክፈፎችን፣ አግዳሚዎችን፣ ቋሚዎችንና መሠረቶችን፤ ታቦቱን ከነመሎጊያዎቹ፣ የስርየት መክደኛውንና የሚሸፍነውን መጋረጃ፤ ጠረጴዛውን ከነመሎጊያዎቹ፣ ዕቃዎቹን ሁሉና የገጸ ኅብስቱን፤ ለመብራት የሆነውን መቅረዝ ከነዕቃዎቹ፣ ቀንዲሎችንና ለመብራት የሚሆነውን ዘይት፤ የዕጣን መሠዊያውን ከነመሎጊያዎቹ፣ ቅብዐ ዘይቱንና ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን፤ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ የሚሆነውን የመግቢያ መጋረጃ፤ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን ከንሓስ መጫሪያው፣ መሎጊያዎቹንና ዕቃዎቹን ሁሉ፣ የንሓስ ሰኑን ከነማስቀመጫው፣ የአደባባዩን መጋረጃዎች ከነምሰሶዎቻቸውና ከነመሠረቶቹ፣ የአደባባዩን መግቢያ መጋረጃ፤ ለመገናኛው ድንኳንና ለአደባባዩ የሚሆኑ የድንኳን ካስማዎችና ገመዶቻቸው፤ በመቅደሱ ውስጥ ለማገልገል የሚለበሱ የፈትል ልብሶችን ይኸውም የካህኑ የአሮንን የተቀደሱ ልብሶችንና ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚለብሷቸውን የወንዶች ልጆቹን ልብሶች ይሥሩ።” ከዚያም የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጡ፤ ፈቃደኛ የነበረና ልቡን ያነሣሣው ሁሉ በመምጣት ለመገናኛው ድንኳን ሥራ፣ ለአገልግሎቱ ሁሉና ለተቀደሱ ልብሶች የሚሆን ለእግዚአብሔር መባ አመጡ።
ዘፀአት 35:10-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በእናንተም ዘንድ ያሉ በልባቸው ጥበበኞች ሁሉ መጥተው እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ያድርጉ። ማደሪያውን፥ ድንኳኑንም መደረቢያውንም፥ መያዣዎቹንም፥ ሳንቆቹንም፥ መወርወሪያዎቹንም፥ ምሰሶቹንም፥ እግሮቹንም፤ ታቦቱን መሎጊያዎቹንም፥ የስርየት መክደኛውንም በእርሱም ፊት የሚሸፍነውን መጋረጃ፤ ገበታውን መሎጊያዎቹንም ዕቃውንም ሁሉ፥ የገጹንም ኅብስት፤ መብራት የሚያበሩበትን መቅረዙን ዕቃውንም፥ ቀንዲሉንም፥ የመብራቱንም ዘይት፤ የዕጣኑን መሠዊያም መሎጊያዎቹንም፥ የቅብዓቱንም ዘይት፥ ጣፋጩንም ዕጣን፥ ለማደሪያውም ደጃፍ የሚሆን የደጃፉን መጋረጃ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያውን፥ የናሱንም መከታ፥ መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፤ የመታጠቢያውን ሰንም መቀመጫውንም፤ የአደባባዩን መጋረጆች ምሰሶቹንም እግሮቻቸውንም፥ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ፤ የማደሪያውን ካስማዎች፥ የአደባባዩንም ካስማዎች አውታሮቻቸውንም፤ በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነት ያገለግሉበት ዘንድ የተቀደሱትን የካህኑን የአሮን ልብሶች፥ የልጆቹንም ልብሶች። የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጡ። ከእነርሱም ሰው ሁሉ ልቡ እንዳነሣሣው መንፈሱም እሺ እንዳሰኘው ለመገናኛው ድንኳን ሥራ ለማገልገያውም ሁሉ ለተቀደሰውም ልብስ ለእግዚአብሔር ስጦታ አመጡ።
ዘፀአት 35:10-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“በእናንተ ዘንድ ያለ፥ በልቡ ጥበበኛ የሆነ ሁሉ መጥቶ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ያድርግ። ድንኳኑንም፥ አደባባዩንም፥ መደረቢያውንም፥ መያዣዎቹንም፥ ሳንቆቹንም፥ መወርወሪያዎቹንም፥ ምሰሶዎችንና እግሮቻቸውን፤ የቃል ኪዳኑን ታቦትም፥ መሎጊያዎቹንም፥ የስርየት መክደኛውንም፥ መጋረጃውንም፤ ገበታውንና መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ ኅብስተ ገጹንም፤ መብራት የሚያበሩበትን መቅረዙን፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ ቀንዲሉንም፥ የመብራቱንም ዘይት፤ የዕጣኑንም መሠዊያ፥ መሎጊያዎቹንም፥ የቅብዐቱንም ዘይት፥ ጣፋጩንም ዕጣን፥ ለማደሪያውም ደጃፍ የሚሆን የደጃፉን መጋረጃ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያውን፥ የናሱንም መከታ፥ መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንም፥ መቀመጫውንም፤ የአደባባዩን መጋረጆች፥ ምሰሶዎችንም፥ እግሮቻቸውንም፥ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ፤ የማደሪያውን ካስማዎች፥ የአደባባዩንም ካስማዎች፥ አውታሮቻቸውንም፤ በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነት ያገለግሉበት ዘንድ የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶች፥ የልጆቹንም ልብሶች።” የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከሙሴ ዘንድ ወጡ። ከእነርሱም ሰው ሁሉ እያንዳንዱ ልቡ እንዳነሣሣው፥ መንፈሱም እሺ እንዳሰኘው ለምስክሩ ድንኳን ሥራ ለማገልገያውም ሁሉ ለመቅደስ ልብስ ለእግዚአብሔር ስጦታ አመጡ።
ዘፀአት 35:10-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“በመካከላችሁ ጥበበኞች የሆኑ ሁሉ መጥተው እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ይሥሩ፦ “የመገናኛውን ድንኳን ከነድንኳኑና ከነመደረቢያው፣ ማያያዣዎችን፣ ክፈፎችን፣ አግዳሚዎችን፣ ቋሚዎችንና መሠረቶችን፤ ታቦቱን ከነመሎጊያዎቹ፣ የስርየት መክደኛውንና የሚሸፍነውን መጋረጃ፤ ጠረጴዛውን ከነመሎጊያዎቹ፣ ዕቃዎቹን ሁሉና የገጸ ኅብስቱን፤ ለመብራት የሆነውን መቅረዝ ከነዕቃዎቹ፣ ቀንዲሎችንና ለመብራት የሚሆነውን ዘይት፤ የዕጣን መሠዊያውን ከነመሎጊያዎቹ፣ ቅብዐ ዘይቱንና ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን፤ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ የሚሆነውን የመግቢያ መጋረጃ፤ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን ከንሓስ መጫሪያው፣ መሎጊያዎቹንና ዕቃዎቹን ሁሉ፣ የንሓስ ሰኑን ከነማስቀመጫው፣ የአደባባዩን መጋረጃዎች ከነምሰሶዎቻቸውና ከነመሠረቶቹ፣ የአደባባዩን መግቢያ መጋረጃ፤ ለመገናኛው ድንኳንና ለአደባባዩ የሚሆኑ የድንኳን ካስማዎችና ገመዶቻቸው፤ በመቅደሱ ውስጥ ለማገልገል የሚለበሱ የፈትል ልብሶችን ይኸውም የካህኑ የአሮንን የተቀደሱ ልብሶችንና ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚለብሷቸውን የወንዶች ልጆቹን ልብሶች ይሥሩ።” ከዚያም የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጡ፤ ፈቃደኛ የነበረና ልቡን ያነሣሣው ሁሉ በመምጣት ለመገናኛው ድንኳን ሥራ፣ ለአገልግሎቱ ሁሉና ለተቀደሱ ልብሶች የሚሆን ለእግዚአብሔር መባ አመጡ።
ዘፀአት 35:10-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በእናንተም ዘንድ ያሉ በልባቸው ጥበበኞች ሁሉ መጥተው እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ያድርጉ። ማደሪያውን፥ ድንኳኑንም መደረቢያውንም፥ መያዣዎቹንም፥ ሳንቆቹንም፥ መወርወሪያዎቹንም፥ ምሰሶቹንም፥ እግሮቹንም፤ ታቦቱን መሎጊያዎቹንም፥ የስርየት መክደኛውንም በእርሱም ፊት የሚሸፍነውን መጋረጃ፤ ገበታውን መሎጊያዎቹንም ዕቃውንም ሁሉ፥ የገጹንም ኅብስት፤ መብራት የሚያበሩበትን መቅረዙን ዕቃውንም፥ ቀንዲሉንም፥ የመብራቱንም ዘይት፤ የዕጣኑን መሠዊያም መሎጊያዎቹንም፥ የቅብዓቱንም ዘይት፥ ጣፋጩንም ዕጣን፥ ለማደሪያውም ደጃፍ የሚሆን የደጃፉን መጋረጃ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያውን፥ የናሱንም መከታ፥ መሎጊያዎቹንም፥ ዕቃውንም ሁሉ፤ የመታጠቢያውን ሰንም መቀመጫውንም፤ የአደባባዩን መጋረጆች ምሰሶቹንም እግሮቻቸውንም፥ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ፤ የማደሪያውን ካስማዎች፥ የአደባባዩንም ካስማዎች አውታሮቻቸውንም፤ በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነት ያገለግሉበት ዘንድ የተቀደሱትን የካህኑን የአሮን ልብሶች፥ የልጆቹንም ልብሶች። የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጡ። ከእነርሱም ሰው ሁሉ ልቡ እንዳነሣሣው መንፈሱም እሺ እንዳሰኘው ለመገናኛው ድንኳን ሥራ ለማገልገያውም ሁሉ ለተቀደሰውም ልብስ ለእግዚአብሔር ስጦታ አመጡ።
ዘፀአት 35:10-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“በመካከላችሁ የሚገኙ የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ እግዚአብሔር ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር ለመሥራት ይምጡ፤ ይኸውም ድንኳኑን፥ የውስጥና የውጪ መደረቢያዎችን፥ መያዣዎችንና ተራዳዎችን መወርወሪያዎችንና ምሰሶዎችን፥ እግሮቹን፥ የኪዳኑን ታቦት፥ መሎጊያዎቹን፥ የስርየት መክደኛውንና የታቦቱ መሸፈኛ የሆነውን መጋረጃ፥ ጠረጴዛውን፥ መሎጊያዎቹንና የእርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ እንዲሁም ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን የተቀደሰ ኅብስት ለመብራት ማኖሪያ የሚሆነውን መቅረዝና የእርሱንም መገልገያ ዕቃዎች፥ መብራቶቹም ከዘይታቸው ጋር፥ የዕጣን መሠዊያውንና መሎጊያዎቹን፥ የቅባቱን ዘይት፥ ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን፥ የድንኳኑን በር መጋረጃ፥ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ፥ የነሐሱንም መከላከያ መሎጊያዎቹንና የእርሱን መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫውን፥ ያደባባዩን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹንና እግሮቻቸውን፥ የአደባባዩን በር መጋረጃዎች፥ የድንኳኑንና የአደባባዩን ካስማዎች፥ አውታሮችና ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ በሚያገለግሉበት ጊዜ የሚለብሱአቸው በጥበብ ያጌጡ ልብሶችን ይኸውም ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ የተሠሩትን የተቀደሱ ልብሶች ይሥሩ።” ከዚህ በኋላም የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጡ፤ ለመሥራት እያንዳንዱ ለመስጠት ልቡ የፈቀደውን ለእግዚአብሔር መባ አመጣ፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን ለመንፈሳዊ አገልግሎት ለካህናት ልብስ የሚሆነውን ነገር ሁሉ አመጡ።
ዘፀአት 35:10-21 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
“በእናንተ መካከል ያሉ በልባቸው ጥበበኞች የሆኑ ሁሉ መጥተው ጌታ ያዘዘውን ሁሉ ያድርጉ። ማደሪያውን፥ ድንኳኑን፥ መደረቢያውን፥ መያዣዎቹን፥ ሳንቃዎቹን፥ መወርወሪያዎቹን፥ ምሰሶዎቹን፥ እግሮቹን፤ ታቦቱንና መሎጊያዎቹን፥ የስርየት መክደኛውን፥ መሸፈኛ መጋረጃ፥ ገበታውና መሎጊያዎቹን፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ ኅብስተ ገጹን፥ መብራት የሚያበሩበትን መቅረዝና ዕቃውን፥ ቀንዲሉን፥ የመብራቱን ዘይት፤ የዕጣኑን መሠዊያና መሎጊያዎቹን፥ የቅባቱን ዘይት፥ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን፥ የድንኳኑን ደጃፍ መጋረጃ፤ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያና የነሐሱን መከታ፥ መሎጊያዎቹንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫውን፤ የአደባባዩን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹንና እግሮቻቸውን፥ የአደባባዩን ደጃፍ መጋረጃ፤ የማደሪያውን ካስማዎች፥ የአደባባዩን ካስማዎችና አውታሮቻቸውን፤ በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነት እንዲያገለግሉበት የተቀደሱትን የካህኑን የአሮን ልብሶችና የልጆቹን ልብሶች።” የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጡ። ልቡ ያነሣሣውና መንፈሱ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ ሰው ሁሉ ለመገናኛው ድንኳን ሥራና ለአገልግሎቱ ሁሉ ለተቀደሰውም ልብስ የሚሆን ለጌታ ስጦታ አመጡ።