መርዶክዮስ እንደ ልጁ አድርጎ ያሳደጋት የአጎቱ የአቢካኢል ልጅ አስቴር ወደ ንጉሡ ዘንድ የምትሄድበት ተራ በደረሰ ጊዜ የሴቶች ልዩ ጥበቃ ቤት ኀላፊ የሆነው ሄጌ የነገራትን እንጂ፣ ሌላ ምንም አልጠየቀችም። አስቴር በሚያዩዋት ሁሉ ዘንድ ሞገስ አገኘች። በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ቴቤት በተባለው በዐሥረኛው ወር አስቴር ወደ ንጉሥ ጠረክሲስ ቤተ መንግሥት ተወሰደች። በዚህ ጊዜ ንጉሡ ከሌሎቹ ሴቶች ሁሉ ይበልጥ አስቴርን ወደዳት፤ ከሌሎቹ ደናግልም ሁሉ ይልቅ በርሱ ዘንድ ሞገስንና መወደድን አገኘች። ስለዚህ የእቴጌነት ዘውድ በራሷ ላይ ጫነላት፤ በአስጢንም ፈንታ ንግሥት አደረጋት። ንጉሡም ስለ አስቴር ክብር ለመኳንንቱና ለሹማምቱ ሁሉ ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ በዓሉም በየአውራጃዎቹ ሁሉ እንዲከበር ዐወጀ፤ በንጉሣዊ ልግስናውም ስጦታ አደረገ። ደናግሉ ለሁለተኛ ጊዜ ተሰብስበው ሳለ፣ መርዶክዮስ በንጉሡ በር ተቀምጦ ነበር። አስቴር ግን ልክ መርዶክዮስ እንደ ነገራት የማን ወገንና የየት አገር ሰው እንደ ሆነች ደብቃ ነበር፤ ይህ የሆነበት ምክንያት መርዶክዮስ በሚያሳድጋት ጊዜ ታደርግ እንደ ነበረው ሁሉ፣ አሁንም ምክሩን ትከተል ስለ ነበር ነው። መርዶክዮስ በንጉሡ በር ተቀምጦ ሳለ፣ በሩን ከሚጠብቁት ከንጉሡ የጦር አለቆች ሁለቱ ገበታና ታራ ተቈጡ፤ ንጉሥ ጠረክሲስንም ለመግደል ዶለቱ። መርዶክዮስም አድማውን ስለ ደረሰበት፣ ለንግሥት አስቴር ገለጸላት፤ እርሷም ይህን ከመርዶክዮስ ማግኘቷን ለንጉሡ ገልጻ ነገረችው። ነገሩ ሲጣራም እውነት ሆኖ ተገኘ፤ ሁለቱም ሹማምት በስቅላት ሞት ተቀጡ። ይህ ሁሉ በንጉሡ ፊት በታሪክ መዝገብ ተጻፈ።
አስቴር 2 ያንብቡ
ያዳምጡ አስቴር 2
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: አስቴር 2:15-23
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች