ከጥቂት ጊዜ በኋላም የሶርያ ንጉሥ ቤን ሃዳድ ሰራዊቱን ሁሉ ሰበሰበ፤ ወጥቶም ሰማርያን ከበባት። ከተማዪቱን እንደ ከበባትም የአንድ አህያ ጭንቅላት በሰማንያ ሰቅል ብር፣ የጎሞር አንድ ስምንተኛ የርግብ ኵስ በዐምስት ሰቅል ብር እስኪሸጥ ድረስ ታላቅ ራብ ሆነ። የእስራኤልም ንጉሥ በቅጥሩ ላይ በሚመላለስበት ጊዜ አንዲት ሴት፣ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ “ጌታዬ፣ ንጉሥ ሆይ፤ እባክህ ርዳኝ!” አለች። ንጉሡም፣ “እግዚአብሔር ካልረዳሽ እኔ እንዴት ልረዳሽ እችላለሁ? ከዐውድማው ነው ወይስ ከወይን መጥመቂያው የምረዳሽ?” ሲል መለሰላት። ከዚያም፣ “ለመሆኑ ችግርሽ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃት። እርሷም እንዲህ ስትል መለሰችለት፤ “ይህች ሴት፣ ‘ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪው፤ ነገ ደግሞ የእኔን ልጅ እንበላዋለን’ አለችኝ። ስለዚህ ልጄን ቀቅለን በላነው። በማግስቱም፣ ‘እንድንበላው ልጅሽን አምጪው’ አልኋት፤ እርሷ ግን ደበቀችው።” ንጉሡም ሴቲቱ ያለችውን ሲሰማ ልብሱን ቀደደ፤ በቅጥሩ ላይ በሚመላለስበትም ጊዜ፣ ማቅ ከውስጥ መልበሱን ሕዝቡ አየ። ንጉሡም፣ “የሣፋጥ ልጅ የኤልሳዕ ራስ ዛሬ በዐንገቱ ላይ ካደረ፣ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ከዚህም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ዛተ። በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በቤቱ ተቀምጦ ነበር፤ ሽማግሌዎችም ዐብረውት ተቀምጠው ነበር። ንጉሡም መልእክተኛ ቀድሞት እንዲሄድ አደረገ። የተላከውም ሰው ከመድረሱ በፊት ኤልሳዕ ለሽማግሌዎቹ፣ “ይህ ነፍሰ ገዳይ ራሴን ለመቍረጥ ሰው መላኩን ታያላችሁ? እነሆ፤ አሁንም መልእክተኛው ሲደርስ በሩን ዘግታችሁ እንዳይገባ አድርጉ። የጌታው የእግሩ ኮቴ ከኋላው ይሰማ የለምን?” አላቸው። ኤልሳዕ ከሽማግሌዎቹ ጋራ በመነጋገር ላይ ሳለም፣ መልእክተኛው ወደ እርሱ ወረደ። ንጉሡም ደርሶ፣ “ይህ ጥፋት የመጣው ከእግዚአብሔር ነው፤ ታዲያ እኔ ከእግዚአብሔር ምን እጠብቃለሁ?” አለ።
2 ነገሥት 6 ያንብቡ
ያዳምጡ 2 ነገሥት 6
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 2 ነገሥት 6:24-33
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos